የአጼ ዳዊት ዋሻዎች

ከ1375- 1380 ዐ.ም የ አጼዘረያቆብ አባት በነበሩት በ አጼዳዊት ተሰራ፡፡ ዋሻው በኮከብ ቅርጽ የተሰሩ 3 ክፍሎች ያሉት ከአንድ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ ነው፡፡ በአጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት የንጉሱ ውድ እቃዎች ማስቀመጫነት ያገለግል የነበረ ሲሆን በ15 ኛው ክ/ ዘመን የግራኝ አህመድ ወታደሮች እንደ ምሽግ ተጠቅመዉበታል፡፡ በአጼ ምኒልክ ዘመን የቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን ከመሰራቱ በፊት የታቦቱ ማኖርያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በእንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስትያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡