የካቲት ፲፩
(ከየካቲት 11 የተዛወረ)
የካቲት ፲፩፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፷፩ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፵፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፭ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፬ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፫፻፳፬ ዓ/ም - ቀዳማዊ አጼ አምደ ጽዮን በደቡብ ኢትዮጵያ እስላማዊ ግዛቶችን ለማስገበር ዘመቱ።
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ለራስ ወልደ ጊዮርጊስአቦዬ ዘውድ ጭነውላቸው ንጉሠ ዘቤጌምድርና ስሜን አድርገው ሾሟቸው።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት የመምህራን አድማ ተደረገ። ከዚህም ጋር አብሮ የአዲስ አበባ ታክሲ ነጅዎች አድማ አደረጉ። የታክሲ ነጅዎቹ አድማ ለስድስት ቀናት ቆየ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትን መስከረም ፪ ቀን የገለበጠውን፣ የኅብረተ ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር (ደርግ) ለመገርሰስ፣ በቀድሞ አጠራሩ ተጋድሎ ሓርነት ሕዝብ ትግራይ (ተሓሕት"፣ በኋላም ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ተመሠረተ፤ በምዕራባዊ ትግራይ ደደቢት በተባለ ሥፍራም የትጥቅ ትግሉን ጀመረ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ደራስያን አንድነት ማኅበር (ኢደአማ) ስሙን ወደ የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) የለወጠበት ዕለት።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከልዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልድ ቂርቆስ፤ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ” (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)፣
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1829
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |