የመርስ ቫይረስ ተስቦ
የመርስ ቫይረስ ተስቦ (እንግሊዝኛ፦ መርስ MERS = «የመካከለኛው ምሥራቅ ሳንባ በሽታ») ከሚያዝያ 2004 ዓ.ም. ጀምሮ የሚታይ የተላላፊ ቫይረስ ተስቦ ነው። ቫይረሱ የተራ ጉንፋን ዝርያ ሲሆን በተለይ ከትኩሳት ጋር ትንፋሽ የሚወስድ አይነት ነው።
እስከ ግንቦት 2006 ዓ.ም. ድረስ ቢያንስ 314 ሰዎች ያህል ገድሏል፤ በጠቅላላ ድምር 813 ሰዎች ታምመዋል።[1] መጀመርያው ቫይረሱ በሚያዝያ 2004 የተገኘው በሳዑዲ አረቢያ ነበር። አብዛኞቹ ህመምተኞች (700 በግንቦት 2006) እና አብዛኞቹ እረፍቶች (ቢያንስ 284) በዚያ ሀገር ሆነዋል።
ይህ ቫይረስ ከሌት ወፍ ወደ ግመል፣ ከግመልም ወደ ሰው ልጅ እንደ ተላለፈ ይታስባል። ባለፈው የካቲት በተገረገው ምርመራ መሠረት፣ በሳዑዲ ውስጥ 74 ከመቶ ግመሎች የቫይረሱን ተሸካሚዎች ናቸው።[2] የሳዑዲ መንግሥት ኗሪዎቹ የግመል ወተት እንዳይጠጡ የሚል ተግሳጽ አስታውቋል።
ከሳዑዲ በኋላ በጆርዳን (ሚያዝያ 2004)፤ ቃጣር፣ እንግሊዝ ( የካቲት 2005)፤ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ቱኒዚያ (ግንቦት 2005)፤ ኦማን (ጥቅምት 2006)፤ ስፔን (ኅዳር)፤ የተባበሩት የዓረብ ግዛቶች፤ ፊሊፒንስ፣ ግሪክ አገር፣ ማሌዢያ፣ ግብጽ (ሚያዝያ)፤ አሜሪካ (ኢንዲያና፣ ፍሎሪዳ፤ ኢሊኖይ)፣ ኢንዶኔዥያ(?)፣ ሆላንድ፣, ሊባኖስና ኢራን (ግንቦት) ተገኝቷል።
በዓለም ዙሪያ፦
- ግንቦት 2005 - 44 ኅመምተኞች፣ 22 እረፍቶች
- ሰኔ 2005 - 60 ኅመምተኞች፤ 38 ዕረፍቶች
- እስከ ግንቦት 2006 ድረስ - 813 ኅመምተኞች፣ ቢያንስ 314 እረፍቶች
ብዙዎቹ የታመሙት ሰዎች በሳዑዲ ውስጥ ሲሆኑ ከነዚህ 80 ከመቶ ወንዶች ናቸው። ምክንያቱም በሳዑዲ ባሕል አብዛኞች ሴቶች አፋቸው አፍንጫቸው ላይ መሸፈኛ ስላለ ነው።
ተስቦው በተለይ በሳዑዲ ስላለ የዓለምም ሙስሊሞች ለሃጅ በረመዳን የሚሄዱት ወደ መካ ስለ ሆነ ይህ አሁን ለዓለም ጤነኞች እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ሆኖአል።
- ^ ፍሉ ትራከርስ
- ^ "MERS coronavirus in 74% of Saudi Arabian camels". Archived from the original on 2014-05-28. በ2014-05-14 የተወሰደ.