ረመዳን
ረመዳን በሂጅራ አቆጣጠር ዘጠነኛው ወር እና በሙስሊሞች ዘንድ የጾም፣ ጸሎት ወር ነው ፡፡ [1] ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዐዘናት ዉስጥ አንዱ ነው ። [2] እና ሃያ ዘጠኝ ወይም ሠላሳ ቀናት ይቆያል ። [3] [4]
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ ምትጠልቅ ድረስ መጾም ለአቅመ አዳም (ሄዋን) ለደረሱ ሙስሊሞች ፋርድ (ግዴታ) ነው ። የክሮኒክ በሽተኞች , መንገደኞች, አረጋውያን, ጡት አጥቢ እናቶች, የስኳር በሽተኞች, ወይም የወር አበባ ያላቸው እንስቶች ሲቅሩ [5] ከሱቢህ ( ፈጅር) አዛን ቀደም ብሎ በለሊት(ንጋት) ላይ የሚበላው ምግብ ሱሁር, እና ምሽት ከመግሪብ አዛን ቡሃላ የሚፈታበት(ሚፈጠርበት) ምግብ ኢፍጣር ይባላል ። [6] [7]
የጾም መንፈሳዊ ሽልማቶች ( ሰዋብ ) በረመዳን ውስጥ እንደሚባዙ ይታመናል ፡ [8] በዚህ መሠረት, ሙስሊሞች ከምግብ እና መጠጥ ብቻ ሳይሆን፣ ከትምባሆ ምርቶች, ከባለቤታቸው ጋር ፆታዊ ግንኙነት፣ እንዲሁም ከመጥፎ ባህሪ ይቆጠባሉ ። [9] [10] ይልቁንስ ሰላት እና ቁርኣን ምቅራትን ያበዛሉ ። [11] [12]
የሃይማኖት ተግባራት
ለማስተካከልየተለመደው ተግባር ከንጋት እስከ ፀሐይ መጥለቅ መፆም ነው ፡፡ ከጾም በፊት የቅድመ-ጎህ ምግብ ሱሁር ሲባል፣ ጻሃይ ስትጠልቅ ጾም የሚፈታበት ምግብ ኢፍጣር ይባላል ። [13]
ሙስሊሞች ብዙ ጊዜን በጸሎት፣ በሰላት እና በሰደቃ(ምጽዋት) እንዲሁም ስነ ምግባራቸውን ለማሻሻል በመጣር ያሳልፋሉ ። [14] [15] ይህም ከታች ባለው ሃዲስ "ረመዳን ሲደርስ የገነት በሮች ይከፈታሉ፣ የሲኦል (ገሃነም) በሮች ይዘጋሉ እና ሰይጣናት ይታሰራሉ ። ” [16]
ባህላዊ ልምዶች
ለማስተካከልየጤና ውጤቶች
ለማስተካከልረመዳን በአግባቡ ከተጾመና በቂ ፈሳሽ በቀን ውስጥ ማግኘት ከተቻለ፣ ጠቃሚ የጡንቻ ክምችቶች ሳይቃጠል ኪሎ መቀነስ ስለሚያስችል የጤና በረከትም ያስገኛል ። [17]
ማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- ^ "Ramadan: Fasting and Traditions".
- ^ "Schools – Religions".
- ^ "Sahih Bukhari – Book 031 (The Book of Fasting), Hadith 124.".
- ^ "Sahih Muslim – Book 006 (The Book of Fasting), Hadith 2378.".
- ^ Fasting (Al Siyam) – الصيام – p. 18, el Bahay el Kholi, 1998
- ^ Islam, Andrew Egan – 2002 – p. 24
- ^ Dubai – p. 189, Andrea Schulte-Peevers – 2010
- ^ Bukhari-Ibn-Ismail, AbdAllah-Muhammad. "Sahih Bukhari – Book 031 (The Book of Fasting), Hadith 125.". hadithcollection.com. Archived from the original on 2013-01-15. በ2021-02-13 የተወሰደ.
- ^ Smith, Jane I.. Islam in America. https://books.google.com/books?id=Tom-AwAAQBAJ&pg=PA15 በ30 May 2017 የተቃኘ.
- ^ Hotaling, Edward. Islam Without Illusions: Its Past, Its Present, and Its Challenge for the Future. https://archive.org/details/islamwithoutillu0000hota በ30 May 2017 የተቃኘ.
- ^ Abu Dawud-Ibn-Ash'ath-AsSijisstani, Sulayman. "Sunan Abu-Dawud – (The Book of Prayer) – Detailed Injunctions about Ramadan, Hadith 1370". Center for Muslim-Jewish Engagement of The University of Southern California.
- ^ Bukhari-Ibn-Ismail, AbdAllah-Muhammad. "Sahih Bukhari – Book 031 (The Book of Fasting), Hadith 199.". hadithcollection.com. Archived from the original on 2013-01-15. በ2021-02-13 የተወሰደ.
- ^ "Ramadan".
- ^ "Book of Fasting – Sahih al-Bukhari – Sunnah.com – Sayings and Teachings of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم)".
- ^ "Sahih Muslim Book 006, Hadith Number 2361.". Archived from the original on 2015-06-04. በ2021-02-13 የተወሰደ.
- ^ "Muslims observe Ramadan, clerics explain significance".
- ^ https://www.bbc.com/amharic/news-44128047