ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 25
- ፲፭፻፷ ዓ.ም. - የዓፄ ልብነድንግል ሚስት እቴጌ ሰብለ ወንጌል በዚህ ዕለት አመድ በር በምትባል ሥፍራ አረፉ።
- ፲፮፻፲፪ ዓ.ም. ሠላሣ ስምንት ከብሪታንያ የመጡ አቅኝዎች ቨርጂኒያ ላይ አርፈው ለ እግዚአብሔር ምስጋናቸውን አቀረቡ። ይሄም ድርጊት በአሜሪካ የመጀመሪያው የምሥጋና ሰርዐት ዕለት ነበር ይባላል።
- ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. በአሜሪካ የሕዝብ እንደራሴዎች ‘United States Senate’ አባላት በስድሳ አምሥት ለ ሰባት ድምጽ አሜሪካ ጥቅምት ፲፬ ቀን ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. የተመሠረተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል እንድትሆን አጸደቁ።
- ፲፱፻፸ ዓ.ም. የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት ጃን ቤደል ቦካሳ ዕራሳቸውን በራሳቸው ቀዳማዊ ቦካሳ በሚል ስም በማንገሥ የአገሪቱም ስም ተቀይሮ ‘የመካከለኛው አፍሪካ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት’ በሚል ስም ተሰየመች።
- ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. በሶማሊያ አገር ውስጥ በተከሰተው የ’ዕርስ በርስ ጦርነት’ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ጆርጅ ኸርበርት ዎከር ቡሽ የ’ሰብዓዊ ርሕራሔ’ ምክንያት በሚል መነሻ ሃያ ስምንት ሺህ የአሜሪካ ወታደሮችን ወደ ሶማሊያ ላኩ።