ሳምሱ-ኢሉና ከ1662 እስከ 1624 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የባቢሎን 7ኛ ንጉሥ ነበረ። አባቱን ሃሙራቢን ተከተለው።

ለሳምሱ-ኢሉና ዘመን 38 ያህል የዓመት ስሞቹ ታውቀዋል። እንግዲህ በ9ኛው ዓመት (1654 ዓክልበ.) ካሳውያንን እንዳሸነፈ ታውቋል። በሚከተለው ዓመት የላርሳ ገዥ 2 ሪም-ሲን በዓመጽ ተነሣ፣ ይህም አመጽ በመላው ሱመርና አካድ ተስፋፋ። ሳምሱ-ኢሉና ግን እስከ 1649 ዓክልበ. ድረስ አመጸኖቹን ሁሉ አጠፋቸው። ከዚህ በኋላ ግን የኢሲን ገዥ ኢሉማ-ኢል በአመጽ ተነሣ፣ ደቡብም ሱመር በኢሊማ-ኢል ሥር «የባሕር-ምድር» የሚባለው ግዛት ሆነ (1645-1463 አክልበ. ግድም)።

በ፳ኛው አመት (1643 ዓክልበ.) ኤሽኑና እንደገና ባመጸ ጊዜ ሳምሱ-ኢሉና አመጹን አጠፋ። በ1635-34 ዓክልበ. ፪ አሞራውያን ነገሥታት ያዲሀቡምና ሙቲ-ሑርሻን አሸነፋቸው። በ1628 ዓክልበ. ደግሞ አሞራውያንን አሸነፋቸው።

የሳምሱ-ኢሉና ተከታይ ልጁ አቢ-ኤሹሕ ነበረ።

ቀዳሚው
ሃሙራቢ
ባቢሎን ንጉሥ
1662-1624 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አቢ-ኤሹሕ

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል