የአዋን ሥርወ መንግሥት እስከሚታወቅ ድረስ የኤላም መጀመርያ ሥርወ መንግስት ሲሆን የታሪካዊ መዝገቦች መጋረጃ ከተከፈተበት ወቅት ጀምሮ ተገኝቶ ነበር። «አዋን» ምናልባት ከሱስን ሩቅ ያልሆነ አገር ወይም ከተማ ስም ነበረ።

የአዋንና የሲማሽኪ ሥርወ ነገስታት ዝርዝር ሰነድ

ኤላም ከጥንት ጀምሮ የሱመር ከተሞች ተዋዳዳሪ ነበረ። ከሥነ ቅርስ የታወቀው የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ ኤላምን እንዳሸነፈው ተባለ። ከዚህ በኋላ የኡሩክና የኡር ነገሥታት በተራቸው የሱመር ላዕላነቱን ይዘው ነበር። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ ኡር ወደቀና ላዕላይነቱ ወደ አዋን ነገሥታት ተዛወረ።

ሦስት የአዋን ነገሥታት በሱመር ለ356 ዓመታት እንደ ነገሡ ሲል ይህ ቁጥር ግን ሊታመን አይችልም፤ ከዚህ በላይ የነገሥታቱ ስሞች ከጽላቶቹ ጠፍተው አልተገኙም።[1] ሦስተኛው ስም በከፊል «ኩ-ኡል-...» ለ36 አመት እንደነገሠ ብቻ ከአንድ ቅጂ ሊነብ ይችላል።[2] የአዋን ነገሥታት በጣም ረጅም ለሆነ ጊዜ በሱመር እንደ ታገሡ የማይመስል ነው። በመጨረሻ በኪሽ አዲስ ሥርወ መንግሥት እንደ ተነሣ ላዕላይነቱን ከአዋን እንደ ያዘ ይለናል።

በሱስን አንድ ሰነድ ተገኝቶ 12 የአዋን ነገሥታት ስሞች ይሰጣል።[3] ለዚህ ዘመን ያሉት ምንጮች እጅግ ጥቂት ስለ ሆኑ፣ እኚህ ስሞች በብዛት እርግጥኛ አይደሉም።

በዚህ ጊዜ ኤላም ከሱመር እህል ያስገባ ሲሆን፣ ወደዚያ በሬሱፍባርያብር ያስወጣ ነበር። በአንድ ሰነድ መሠረት፣ ቆርቆሮ ከሱመር ወደ ኤላም ተልኮ እንደ ነሐስ ይመልስ ነበር።

ሌላ ጽላት እንደሚለን፣ በላጋሽ ገዢ ኤነታርዚ ዘመን፣ 600 ኤላማዊ ሌቦች ከላጋሽ ምርኮ ይዘው ሲያመልጡ ተሸነፉ።

አካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ዘመን፣ የኤላምን ንጉሥ ሉህ-ኢሻን፣ የሂሺፕራሺኒ ልጅ ሲያሸንፍ ምርኮ ከአዋን እንደ ያዘ የሚነግሩን መዝገቦች አሉ። ይህ ሉህ-ኢሻን በአዋን ነገሥታት ዝርዝር ላይ 8ኛው ነው፤ የአባቱም ሂሺፕራሺኒ ስም በአዋን ነገሥታት ዝርዝር የ9ኛው ንጉስ ሂሸፕራተፕ ስም ይመስላል።[2]

የሳርጎን ልጅና ተከታይ ሪሙሽ ደግሞ ኤላምን፤ ንጉሱንም ኤማህሲኒ እንዳሸነፈው ተባለ። የኤላምና የማርሃሺ ሃያላት በጦር አለቃ ሲድጋው ሥር ሆነው ከአዋንና ከሱስን መካከል ባለው ወንዝ አጠገብ በሆነ ውግያ ተሸነፉ። ከዚህ በኋላ የሱስን አውራጃ ለአካድ መንግሥት ተገዥ ሆነ። አንድ ውል በኤላምኛ ከአካድ ንጉሥ ናራም-ሲንና ስሙ ካልታወቀ የአዋን ገዢ መካከል ተገኝቷል።

አዋን ምንም ቢሸነፍም ኤላማውያን በአካድ በሙሉ አልተዋጡም። አካዳውያን አንሻንን መቸም አልደረሱምና የኤላም ዋና ከተማ ሆነ።

የአካድ መንግሥት በደከመበት ሰዓት የሱስን ገዢ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ነጻነቱን አዋጀ። ከዚህ በኋላ አዋንንና ሲማሽኪን ወደ ግዛቱ ጨመረ። በአዋን ነገሥታት ዝርዝር ላይ የመጨረሻው ንጉሥ ስም ነው። ኤላምን በሙሉ ከያዘ በኋላ በሱመር ውስጥ ዘመተ፣ በዚያ ኤሽኑናን እና አካድን ያዘ።

ኡር ንጉሥ ኡር-ናሙ በኋላ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ድል አደረገ።[4] ስለዚህ ከአካድና ከኡር-ናሙ መካከል የገዙት ጉታውያን ለ124 አመት እንደ ቆዩ አይቻልም፤ ሌላ ምንጭ እንደሚለው ለ25 አመት ብቻ እንደ ነበር ያስረዳል።

ከኩቲክ-ኢንሹሺናክ ዘመን በኋላ የአዋን ስም አንድ ጊዜ ብቻ ይመዘገባል፤ ነገር ግን ከዚህ በፊት የአንሻን ስም አንድ ጊዜ ብቻ ሲታይ ከላጋሽ ንጉሥ ጉደአ በኋላ ተራ ይሆናል። ስለዚህ ምናልባት የአንሻንና የአዋን ወሰኖች አንድላይ እንደ ነበሩ የሚል አሣብ አለ።[5]

ከኩቲክ-ኢንሹንሺናክ ድል በኋላ (1979 ዓክልበ. ግድም) የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት በኤላም ተነሣ።

የአዋን ነገሥታት ዝርዝር

ለማስተካከል
  1. ፔሊ፣
  2. ታታ፣
  3. ኡኩ-ታንሂሽ፣
  4. ሂሹታሽ፣
  5. ሹሹን-ታራና፣
  6. ናፒ-ኢልሁሽ፣
  7. ኪኩ-ሲወ-ተምቲ፣
  8. ሉሂ-ኢሻን (በታላቁ ሳርጐን ዘመን የነገሠ)
  9. ሂሸፕ-ራተፕ፣
  10. ሔሉ፣
  11. ሒታ፣
  12. ኩቲክ-ኢንሹሺናክ (በኡር-ናሙ ዘመን ነገሠ)
ቀዳሚው
የለም?
ኤላም አለቆች
2429-2070 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
አካድ ንጉሥ ሳርጎን
ቀዳሚው
ዑር ንጉሥ መስኪአጝ-ኑና
ሱመር አለቆች (3)
2310-2274 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኪሽ ንጉሥ ካልቡም
  1. ^ Legrain, 1922, pp. 10, 12, 22.
  2. ^ "Encyclopedia Iranica, "AWAN"". Archived from the original on 2010-12-08. በ2011-03-20 የተወሰደ.
  3. ^ Cameron, 1936; Hinz, 1972; The Cambridge Ancient History; Vallat, 1998.
  4. ^ Wilcke; See Encyclopedia Iranica articles AWAN, ELAM
  5. ^ see Hansman; Encyclopedia Iranica, "Anshan".

ዋቢ መጻሕፍት

ለማስተካከል