የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥት

(ከሲማሽኪ የተዛወረ)

የሲማሽኪ ሥርወ መንግሥትኤላም (አሁን ፋርስ) ከአዋን ሥርወ መንግሥት በኋላ (1979-1858 ዓክልበ. ግድም) የተነሡት ነገስታት ናቸው። «ሲማሽኪ» ከተማ ምናልባት በአሁኑ እስፋሃን አካባቢ ሲሆን ግዛቱ ወደ ስሜን ምናልባት እስከ ካስፒያን ባህር ድረስ ጠቀለለ።

የአዋንና የሺማሽኪ ነገስታት የሚዘረዝረው ጽላት

የአዋን መጨረሻ ንጉሥ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ሲማሽኪን ይዞ ነበር፤ በ1979 ዓክልበ. ግድም በኡር-ናሙ ተሸንፎ ሲማሽኪ በራሱ ንጉሥ ጊርናሜ ሥር እንደገና ነጻ ሆነ። የአዋንን ነገሥታት የሚዘረዝረው ጽላት ደግሞ ፲፪ የሲማሽኪ ነገሥታት ስሞች አለው። ከነዚህ ፲፪ቱ ነገስታት፣ ፱ኞቹ ከሌሎች ሰነዶችና ቅርሶች ይታወቃሉ። ብዙ ጊዜ ከዑር መንግሥት ይታገሉ ነበር። በ1901 ዓክልበ. ግድም ስድስተናው የሺማሽኪ ንጉሥ ኪንዳቱ ሱሳንንና አንሻንን ከዑር ግዛት ያዛቸው። ከ1893 እስከ 1888 ዓክልበ. ድረስ የዑር ንጉሥ ኢቢ-ሲን ሲማሽኪን አሸንፎ ወደ ዑር መንግሥት ጨመረው፤ መላውን አገሩን በደንብ ማቆጣጠር እንደ ተቻለው ግን አይመስልም። በ1879 ዓክልበ. ኪንዳቱና የኤላማውያን ሥራዊት ዑርን በዘበዙና የዑርን መንግሥት አስጨረሱት። በሚከተለው ዓመት ግን የኢሲን ንጉሥ እሽቢ-ኤራ ከኡር አባረራቸው። ፱ኛው የሲማሽኪ ንጉሥ 2 ኤፓርቲ በ1858 ዓክልበ. ግድም አዲስ የኤፓርቲ ሥርወ መንግሥት መሠረተ። ከዚህ በኋላ መጨረሻ ፫ የሲማሽኪ ገዦች በሱሳን ሲነግሡ ለኤፓርቲ ነገሥታት ተገዥ ነበሩ።

የሲማሽኪ ነገሥታት ዝርዝር ለማስተካከል

 1. - ጊርናሜ - በኡር ንጉሥ ሹልጊ ዘመን
 2. - ፩ ታዚታ - በኡር ንጉሥ አማር-ሲን ዘመን
 3. - ፩ ኤፓርቲ - በኡር ንጉሥ ሹ-ሲን ዘመን
 4. - ፪ ታዚታ
 5. - ሉራክ-ሉሃን (፩ ታን-ሩሁራተር)
 6. - ኪንዳቱ (፩ ሁትራን-ተፕቲ፤ ቤቢ) - በዑር ንጉሥ ኢቢ-ሲን ዘመን
 7. - ፩ ኢዳዱ
 8. - ፪ ታን-ሩሁራተር - በኢሲን ንጉሥ ሹ-ኢሊሹ ዘመን
 9. - ፪ ኤፓርቲ - በኢሲን ንጉሥ ኢዲን-ዳጋን ዘመን፤ የኤፓርቲ ሥርወ መንግሥት መሠረተ
 10. - ፪ ኢዳዱ - የኤፓርቲዶች ገዥ (ሱካል) በሱሳን
 11. - ኢዳዱ-ናፒር - " " "
 12. - ኢዳዱ-ተምቲ - " " "