አብርሐም
አብርሃም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት በዑር ከላውዴዎን አብራም ተብሎ ተወልዶ በኋላ ወደ ካራንና ወደ ከነዓን ግብፅም የሄደው የዕብራውያንና፣ የእስማኤላውያን የብዙ ሕዝቦች አባት ነበረ።
አብርሃም | |
---|---|
ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚገኝ የመስኮት ሥዕል አዲስ አበባ | |
የብዙ ሕዝብ አባት | |
የመጀመሪያ ስሙ | አብራም በኋላ አብርሃም |
አባቱ | ታራ |
ባለቤቶቹ |
ሳራ አጋር ዕቁባቱ በመጨረሻም ኩትራ |
ልጆቹ |
እስማኤል ይስሐቅ ዝምራን ጆክሻን ሜዳን ሚዲያን ኢሽባክ ሹሃ |
ወንድሞቹ |
ሃራን ነሆር የአጎቱ ልጅ ሎጥ |
የትውልድ ቦታ | ዑር ከላውዴዎን |
ያረፈበት ቦታ | ኬብሮን |
ያስከተለው | የአይሁድ ክርስትናና እስልምና ሃይማኖት |
የአብርሃም ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ አብርሃም ሕይወት ብዙ ምዕራፍ ይሰጣል።
የአብርሃም ዕድሜ በመጽሐፈ ኩፋሌ
ለማስተካከል- 1876 ዓመተ ዓለም (ዓ.ዓ.) - አብራም ለአባቱ ታራ እና ለእናቱ ኤድና በዑር ከላውዴዎን ተወለደ።
- 1886 ዓ.ዓ. - ሦራ (በኋላ ሣራ) ተወለደች (?)።
- 1891 ዓ.ዓ. - አብራም ወጣት ሆኖ በከብት የሚስብ ማረሻ ፈጠረ።
- 1903 ዓ.ዓ. - አብራም አባቱን ታራን በጣኦታት ለምን ታምናለህ ብሎ ጠየቀው።
- 1925 ዓ.ዓ. - አብራም ሦራንን አገባት።
- 1932 ዓ.ዓ. - ሎጥ ተወለደ።
- 1936 ዓ.ዓ. - አብራም የዑርን አረመኔ መቅደስ አቃጠለና ወደ ካራን ሸሸ።
- 1950 ዓ.ዓ. - የሰናዖር ንጉሥ አምራፌልና የኤላም ንጉሥ ኮሎዶጎምር የሰዶምን አካባቢ በከነዓን ያዙ።
- 1951 ዓ.ዓ. - እግዚአብሔር አብርሃምን ባረከው፣ አብርሃምም ሰማያዊ ቋንቋ ለመማር ጀመረ።
- 1953 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከካራን ወደ ከነዓን ተጓዛ።
- 1954 ዓ.ዓ. - ኬብሮን በከነዓን ተሠራ።
- 1956 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ግብፅ ሄደ።
- 1961 ዓ.ዓ. - ጣይናስ በግብጽ ተሠራ።
- 1963 ዓ.ዓ. - አብርሃም ወደ ከነዓን ወደ ቤቴል ተመለሰ። ሰዶም በኤላም ላይ አመጸ።
- 1964 ዓ.ዓ. - የነገስታት ጦርነት፦ የአብርሃም ሠራዊት አምራፌልን ወዘተ. አሸነፉ። አብርሃምም በምላሽ ስንኳ አንዳችም ሲባጎ ከሰዶም ንጉሥ እንዳይወስድ አሻፈረኝ ነገረለት ። መልከ ሴዴቅ አብርሃምን ባረከው።
- 1965 ዓ.ዓ. - እስማኤል ተወለደ።
- 1979 ዓ.ዓ. - እሳት ከሰማይ ወርዶ ሰዶምንና ገሞራን አጠፋ። አብርሃም ወደ ቤርሳቤ ሄደ፣ ይስሐቅ ተወለደ።
- 1982 ዓ.ዓ. - እስማኤልና እናቱ ሀጋር ወደ ፋራን ምድረ በዳ ተሰደዱ።
- 2003 ዓ.ዓ. - አብርሃምና ይስሐቅ ወደ ደብረ ጽዮን ተጓዙ፤ ወደ ቤርሳቤ ተመለሱ።
- 2010 ዓ.ዓ. - አብርሃም ከቤርሳቤ ወደ ኬብሮን ተመለሰ።
- 2024 ዓ.ዓ. - ሣራ ዐረፈች፤ ለመቃበርዋም አብርሃም ዋሻ ከኬጢያውያን ሰው ከኤፍሮን ገዛ።
- 2027 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ርብቃን አገባት፣ አብርሃምም ከጡራን አገባት።
- 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብና ኤሳው ለይስሐቅ ተወለዱ።
- 2060 ዓ.ዓ. - አብርሃም አረፈ።