ጣኔዎስ (ዓረብኛ صان /ጻን/፣ ግሪክኛ Τάνις /ታኒስ/) ጥንታዊ የግብጽ ከተማ ነበረ።

የጣኔዎስ ፍርስራሽ አሁን

በግሪኩ ታኒስግብጽኛ ስም ጃነት ወይም ጃን መጣ።

ዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ «ጾዓን» ሲባል በግሪኩ ትርጉም (70 ሊ.) «ታኒስ» ይባላል። ብዙ ጊዜ በአገናዛቢው τάνεως ስለሚታይ፣ በብዙዎች እንደ ቦታው ስም ተቀበለ። በአማርኛውም ትርጉም «ጣኔዎስ» ከዚህ እንደ ደረሰ ይመስላል፣ በኩፋሌ ግን አንዴ «ጣይናስ» ተብሎ ይጻፋል።

ኦሪት ዘኊልቊ 13፡22 «ጾዓን» ከኬብሮን በኋላ 7 ዓመት ተሠራች ሲል ይህ ማለት በሂክሶስ ዘመን ዋና ከተማቸው የሆነው አቫሪስ ሳይሆን አይቀርም። በኋላ ዘመን ከዚህ አጠገብ ፈርዖኑ 2 ራምሴስ አዲስ ዋና ከተማ ፒ-ራምሴስ አሠራ።

ከ1085 ዓክልበ. ግድም ጀምሮ ፈርዖኑ ስመንዴስ ከፒ-ራምሴስ ሥፍራ በ25 ኪሎ. ርቀት ከሆነው ከአዲስ ዋና ከተማ «ጃነት» (ታኒስ) ገዛ። «ታኒስ» ወይም ጣኔዎስ በትክክል ለዚያው ሥፍራ ይጠቀማል፣ ለቀደሙት ዋና ከተሞች አቫሪስንና ፒ-ራምሴስን ይዩ።