ያዕቆብ
ያዕቆብ (ዕብራይስጥ፦ יַעֲקֹב, /የዕቆብ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የይስሐቅና የርብቃ ልጅ ነበረ። የዔሳው መንታ ወንድም ነበር። በሌላ ስማቸው ኤዶምያስ (ዔሳው)ና እስራኤል (ያዕቆብ) የተባሉትን ሁለት ብሔሮች ወለዱ። ያዕቆብ (እስራኤል) ግን የተቀደሠ የመሢህ ዘር ተስፋ ወራሽ ሆነ። ያዕቆብና ሚስቶቹ ከነቁባቶቹ የእስራኤል ፲፪ ነገዶች ወለዱ።
በዕዝራ ሱቱኤል ምዕ. ፬ በአዋልድ መጻሕፍት ዕዝራ የዚህን አለም መጨረሻ ከእግዜር መንግሥት መጀመርያ ምን ይለየዋል ሲጠይቅ፣ መልዐኩ ያዕቆብ ከኤሳው ቀጥሎ እንደ ወጣ (ቅርጭምጭሚት ተጨብጦ) ይከተላል የሚል መልስ ሰጠ።
የያዕቆብ ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ያዕቆብ ሕይወት ብዙ ይጻፋል።
የያዕቆብ ዕድሜ በመጽሐፈ ኩፋሌ
ለማስተካከል- 2046 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ (እስራኤል)ና ዔሳው (ኤዶምያስ) ለይስሐቅ ተወለዱ።
- 2080 ዓ.ዓ. - ዔሳው ርስቱን ለያዕቆብ ለምስር ወጥ ይሸጣል በረሃብ ዘመን
- 2114 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ ያዕቆብ ለዔሳው ስቶ ርስቱን ሰጠው።
- 2115 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ ወደ ካራን ሸሸ፤ ዔሳውም ወደ ሴይር (ኤዶም) ሄደ።
- 2122 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ ልያንና ራሔልን አገባቸው[1]፤ በኲሩ ሮቤል ተወለደ።
- 2124 ዓ.ዓ. - ስምዖን ተወለደ።
- 2127 ዓ.ዓ. - ሌዊና ዳን ተወለዱ።
- 2129 ዓ.ዓ. - ይሁዳ ትወለደ።
- 2130 ዓ.ዓ. - ንፍታሌም ተወለደ።
- 2131 ዓ.ዓ. - ጋድ ተወለደ።
- 2132 ዓ.ዓ. - ይሳኮር ተወለደ።
- 2133 ዓ.ዓ. - አሴር ተወለደ።
- 2134 ዓ.ዓ. - ዛብሎን፣ ዮሴፍ እህታቸውም ዲና ተወለዱ።
- 2135 ዓ.ዓ. - እነያዕቆብ ከካራን ሸሽቶ ወደ ከነዓን ተመለሱ።
- 2143 ዓ.ዓ. - የያዕቆብ ቤተሠብ ኤዊያዊው ኤሞርን አሸነፈ፤ ሴኬም ሠፈር አጠፋ። ብንያም ተወለደ።
- 2148 ዓ.ዓ. - የያዕቆብ ቤተሠብ እንደገና የከነዓንን ነገሥታት በሴኬም አሸነፉ።
- 2162 ዓ.ዓ. - ይስሐቅ አረፈ፤ የያዕቆብ ኃያላት ወንድሙን ዔሳውን አሸነፉ።
- 2171 ዓ.ዓ. - የ፯ ዓመት ረሃብ ጀመረ። (1900 ዓክልበ.)
- 2172 ዓ.ዓ. - እስራኤል በረሃብ ምክንያት ወደ ልጁ ዮሴፍ ወደ ግብጽ ሄደ።
- 2188 ዓ.ዓ. - ያዕቆብ ዓረፈ፣ በከነዓን ተቀበረ።