ኅዳር ፳፰
(ከኅዳር 28 የተዛወረ)
ኅዳር ፳፰ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፰ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፯ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል፲፱፻፴፬ ዓ.ም. የጃፓን ንጉሠ ነገሥት የባሕር ኃይል የአሜሪካንን የሰላማዊ ውቅያኖስ የባሕር ኃይል እና አብሮ የተሰለፈውን የጦር ኃይል በ ሃዋይ ደሴቶች ላይ ባለችው ፐርል ሃርበር ‘Pearl Harbour’ በተሰኘችው ወደብ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ አደጋ ጥላባቸው አሜሪካን የሁለተኛው ዓለም ጦርነት ውስጥ እንድትገባ የገፋፋትን ታሪካዊ ሁኔታ ከሰተች።
፲፱፻፸፪ ዓ.ም. በሮዴዥያ የሽግግር መንግሥትን እንዲያስተዳድሩ የተመረጡት የዊንስተን ቸርችል አማች የነበሩት እንግሊዛዊው ‘ሎርድ ሶምስ’ (Lord Soames) እጩነታቸው ይፋ ተደረገ።
፲፱፻፹፰ ዓ.ም. የአሜሪካ የጠረፍ መንኲራኩር ‘ጋሊሌዎ’ ከምድር በተተኮሰች በስድስት ዓመቷ ጁፒተር ዘንድ ደረሰች።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል፲፱፻፹፮ ዓ.ም. አገራቸውን አይቮሪ ኮስትን ከፈረንሳይ ነጻነቷን ከተቀዳጀችበት ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ በፕሬዚደንትነት የመሩት ፊሊክስ ሁፌ ቧኜ በተወለዱ በ ሰማንያ ስምንት ዓመታቸው አረፉ።