ጁፒተር
ጁፒተር፡ (ምልክት፦) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፕላኔት ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት 5ኛ ( አምስተኛ ) ነው። ከበፊቱ ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ መሬት እና ማርስ የተባሉ ፈለኮች ይገኛሉ። ኸበስተኋላው ደግሞ ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ፕሉቶ የተባሉት ይገኛሉ።
ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በግዝፈቱ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል። ግዙፍ የጋዝ ክምችት እንደሆነ ይታመናል። ይህም የጸሃይን አንድ አንድ ሺኛ ( 1/1000ኛ ) ብቻ ክብደት እንዲኖረው ያደርገዋል። ነገር ግን የሌሎቹን ፈለኮች ድምር ክብደት በሁለት ከግማሽ እጥፍ ( 2.5x) ይሆናል። በረጨቱ ውስጥ የጋዝ ክምችት የሆኑት ፈለኮች ሳተርን፣ ኡራኑስ፣ ነፕቲዩን እና ራሱ ጁፒተር ናቸው። በአብዛሃኛው ሃይድሮጅን ከተባለ ጋዝ እና ሩቡን ( 1/4 ኛውን ) ክብደት ከሚይዘው ሂሊየም ከተባለ ንጥረነገር የተሰራ ነው።
ጁፒተር ስልሳ ሦስት ጨረቃዎች አሏት። ከእነዚህ ውስጥ አራቱ ማለትም አዮ ፣ዩሮፓ፣ ጋኒሜድ እና ካሊስቶ የጋሊሊዮ ጨረቃዎች በመባል ይታወቃሉ።