ኅዳር ፳፫
(ከኅዳር 23 የተዛወረ)
ኅዳር ፳፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፪ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፯፻፺፯ ዓ.ም. ፓሪስ በሚገኘው የእመቤታችን (Notre Dame) ካቴድራል፣ አምባገነኑ ናፖሌዮን ቦናፓርት በፈረንሳይ ከአንድ ሺህ ዓመት በኋላ እራሱን ንጉሠ ነገሥት አድርጎ በማንገሥ ዘውዱን በራሱ ላይ ጫነ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - የአሰብ ወደብ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. አቡ ዳቢ፣ አጅማን፣ ሻርጃ፣ ዱባይ እና ኡም አል ቁዌይን በስምምነት የአረብ ኤሚሬት ሕብረትን መሠረቱ።
ልደት
ለማስተካከል፲፱፻፲፯ ዓ.ም. የቀድሞው አሜሪካዊ ጄኔራል እና በፕሬዚደንት ሪቻርድ ኒክሰን እና በፕሬዚደንት ጄራልድ ፎርድ አስተዳደር የ’ዋይት ሃውስ’ ሥራ አስኪያጅ ፥ በፕሬዚደንት ሮናልድ ሬጋን አስተዳደር ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት አሌክሳንደር ሄይግ