ታኅሣሥ ፯
(ከታኅሣሥ 7 የተዛወረ)
ታኅሣሥ ፯ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፷፱ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፷፰ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፰፻፪ ዓ/ም የፈረንሲስ ንጉሠ ነገሥት ናፖሌዎን ቦናፓርት ከሚስቱ ከንግሥት ጆሴፊን ጋር ተፋታ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም በወንድማማቾች መንግሥቱ ንዋይ እና ገርማሜ ንዋይ የተጸነሰሰው የታኅሣሥ ግርግር መፈንቅለ መንግሥት ኃይል እየተዳከመ በአንጻሩ ደግሞ ተቃዋሚዎቻቸው እያደር እየጎለመሱ መሄዳቸውን የተገነዘቡት ሽብርተኞች በቁጥጥራቸው ላይ የነበሩትን ሃያ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ሚኒስትሮችንና መኮንኖችን ወደ አረንጓዴ ሳሎን ያዛውሩና አልጋወራሹንና አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ለብቻቸው እንዲጠበቁ ያደርጋሉ። ጄነራል ጽጌ ዲቡ ወዲያው ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ሲገደሉ፣ እነ ጄነራል መንግሥቱ የያዟቸውን እስረኞት ረሽነው ለማምለጥ ወሰኑ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታኅሣሥ ግርግር ብርጋዴር ጄኔራል ጽጌ ዲቡ ከተቃራኒ ወገን በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታኅሣሥ ግርግር ማለቂያ ዕለት ሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፤ ራስስዩም መንገሻ፤ ራስ አበበ አረጋይ፤ አቶ መኮንን ሀብተወልድ፤ አባ ሐና ጅማ፤ በጠቅላላው አሥራ አምስት ሰዎች ተረሽነው ሞቱ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም የታኅሣሥ ግርግር ማለቂያ ዕለት የክብር ዘበኛ መኮንን የነበሩት ሻምበል ደረጀ ኃይለ ማርያም ሽብርተኞቹን በመቃወም የቤተ መንግሥቱን አጥር በታንክ ደምስሰው ሲገቡ ከሽብርተኞት ወገን በተተኮሰ ጥይት ተገደሉ። ሻምበል ደረጀ የስመ ጥሩው አርበኛ የኃይለ ማርያም ማሞ ልጅ እና የንጉሠ ነገሥቱ የልጅ ልጅ የልዕልት ሶፊያ ደስታ ባል ነበሩ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/December_16
- (እንግሊዝኛ) http://news.bbc.co.uk/onthisday/hi/dates/stories/december/16/newsid_3258000/3258437.stm
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |