ሰኔ ፳፬
(ከሰኔ 24 የተዛወረ)
ሰኔ ፳፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፬ኛው ቀን ሲሆን የፀደይ (በልግ)ወቅት ፹፱ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፸፩ ቀናት፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፸፪ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - አባ ፍራንሲስኮ ፓላው የተባለ የካቶሊክ ሚሲዮናዊ እና መቶ-ዓለቃ ሆሴ ዮአኪን ሞራጋ የተባሉ የእስፓኝ አቅኚዎች የዛሬዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በተቆረቆረችበት ሥፍራ ላይ የሚሲዮናዊ ቤት አቆሙ።
- ፲፰፻፶፮ ዓ/ም - ደጃዝማች ምኒልክ በዓፄ ቴዎድሮስ ትዕዛዝ ታሥረው ከነበሩበት ከመቅደላ አምባ በሌሊት አምልጠው ወደሸዋ አመሩ።
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተወለዱ በ፸፪ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አርፈው ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ጋና በዚህ ዕለት ሪፑብሊክ ስትሆን ክዋሜ ንክሩማ ፕሬዚደንት ተብለው ንግሥት ኤልሣቤጥ (ዳግማዊት)ን በመተካት የአገሪቱ ርዕሰ-ብሔር ሆኑ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - ታላቁ ኢትዮጵያዊ ምሁር አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተወለዱ በ፸፪ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አረፉ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- (እንግሊዝኛ) http://en.wikipedia.org/wiki/July_1
- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤ የመጀመሪያው ፓትርያርክ (፲፱፻፶፩)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |