ማጉስ
ማጉስ በ1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለው ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና ማዋዕል ዘንድ፣ የኬልቶች (በጋሊያ፣ አሁንም ፈረንሳይ አገር) ሁለተኛ ንጉሥ ነበረ። የሳሞጤስ ልጅና ተከታይ ሲሆን ለ49 ዓመት (ምናልባት 2263-2214 ዓክልበ. ግድም) እንደ ነገሠ ተብሏል። ዜና መዋዕሉም በጋሊያ ብዙ መንደሮች እንዳቆመ ይጨምራል።
በአሁኑ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ሆላንድ፣ ምዕራብ ጀርመንና ስሜን-ምዕራብ ጣልያን ብዙ ከተሞች በጥንት ስማቸው ላይ «-ማጉስ» የሚለውን መድረሻ ስለ ነበረ በዚህ ንጉስ ማጉስ እንደ ተመሰረቱ የሚሉ ደራስያን አሉ። ለምሳሌ፣ በፈረንሳይ ሩዋን (ሮቶማጉስ) እና በእንግሊዝ ቸስተር (ኒዮማጉስ) ከተሞች በማጉስ ተሠሩ ብለው ያምናሉ። ከነዚህ በላይ ብዙ ሌሎች ከተሞች ጥንታዊ ሮማይስጥ ስሞች በዚያ ዙሪያ በ -ማጉስ ጨረሱ። እንዲሁም፦
በፈረንሳይ፦
- አርጌንቶማጉስ - አሁን አርዠንቶን-ሱር-ክሮይዝ
- ካሬንቶማጉስ - ካረንታን
- ብሮኮማጉስ - ብሩማት
- ካቶማጉስ - ካየን
- ካሲኖማጉስ - ሻሰኖን
- ካቱሪጎማጉስ - ሾርዥ
- ኮንዳቶማጉስ - ሚሎ
- ኖዊዮማጉስ - ኒዦን
- ኖዊዮማጉስ ሌክሶዊዮሩም - ሊዜ
- ኖዊዮማጉስ ዌሮማንዱዎሩም - ኖዮን
- ኖዊዮማጉስ ትሪካስቲኖሩም - ንዮን
- ዌርኖማጉስ - ቬርኖን፣ ዑር
- አውግስጦማጉስ ሲልዋኔክቱም - ሰንሊ፣ ዋዝ
- ቄሣሮማጉስ በሎዋኮሩም - ቦቬ
- ዩሊዮማጉስ - አንዤ
- ዊንዶማጉስ - ለ ቪጋን፣ ጋርድ
- ብሪዎማጉስ - ብሪሜ
በእንግሊዝ፦
በምዕራብ ጀርመን (ከራይን ወንዝ ምዕራብ)፦
- ቦርቤቶማጉስ - ቩርምዝ
- ኖዊዮማጉስ ትሬዊሮሩም - ኖይማገን-ድሮን
- ኖዊዮማጉስ ኔሜቱም - ስፓየር
- ማርኮማጉስ - ዲውረን
- ሪጎማጉስ - ሬማገን
- ዱርኖማጉስ - ዶርማገን
- ድሩሶማጉስ - ሜሚንገን
- ዩሊዮማጉስ - ፉለንዶርፍ
ሌሎች፦
- ስኪንጎማጉስ - ኤክሲሌስ፣ ጣልያን
- ቦዲንኮማጉስ - ሞንቴው ዳ ፖ፣ ጣልያን
- ካሚሎማጉስ - ሬዳቫሌ፣ ጣልያን
- ኖዊዮማጉስ ባታዎሩም - ኔመሕን፣ ሆላንድ
ማጉስ እጅግ ጥበበኛ ስለ ነበር አንድ የጠቢቦች ክፍል ስለ ስሙ «ማጉስ» (ብዙ ቁጥር፦ ማጊ) ተነሥቶ እነኚህ ማጊዎች ትምህርታቸውን በፋርስ አገር ተስፋፉና ሰብአ ሰገል እንደ ሆኑ የሚሉ ጸሓፊዎች አሉ።
ቀዳሚው ሳሞጤስ |
የሳሞጤያ (ጋሊያ) ንጉሥ 2263-2214 ዓክልበ. ግድም (አፈታሪክ) |
ተከታይ ሳሮን |