ሮቶማጉስ በአሁኑ ሩዋን በፈረንሳይ አገር የተገኘ የሮሜ መንግሥት ከተማ ነበር። ከሮማውያንም በፊት ኗሪ ኬልቶች ራቶማጎስ ይሉት ነበር። የሮማውያን ከተማ በአውግስጦስ ቄሣር ዘመን ተመሠረተ።
በ3ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም. ከተማው በልማቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነበር። ሮማውያን ታላቅ አምፊቴያትር (እንደ ስታዲዩም ከቤት ውጭ የሆነ ቴያትር) እንዲሁም ታላላቅ የፍልወሃ ባኞዎች ሠርተው ነበር፣ ከዚህ በላይ የአሣ ገበያ እንደ ኖረ ይታወቃል።