ሚያዝያ ፲፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፳፰ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፳፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፴፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፴፯ ቀናት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች ለማስተካከል

  • ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - በምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙት ታንጋኒካ እና የዛንዚባር ደሴት ተዋሕደው አንድ አገር መሠረቱ። ይሄም የተዋሕዶ አገር ከሁለቱም ስም በተውጣጣው አዲሱ ስም ታንዛኒያ ተብሎ ተሰየመ።
  • ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - ከደርግ በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት፣ የፖሊስ አለቆች፤ የቀድሞ ሚኒስትሮችና ባለ ሥልጣናት ታሠሩ።
  • ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሶቪዬት ሕብረት ውስጥ የቸርኖቢል የኑክሊዬር መብራት ኃይል ማምረቻ ክፉ አደጋ ተከሰተ። የዚህን አደጋ ክስተት የስካንዲናቪያ አገሮች ይፋ እስካደረጉት ድረስ የሶቪዬት ሕብረት ባለ ሥልጣናት ደፋፍነውት ነበር።


ልደት ለማስተካከል

ዕለተ ሞት ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ