ሚያዝያ ፫
ሚያዝያ ፫፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፲፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፶፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፶፪ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
ለማስተካከል- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የስቅለት ዓርብ ዕለት በ ሎርድ ናፒዬር የሚመራው የእንግሊዝ ሠራዊት እና የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት በመቅደላ ተራራ ሥር በምትገኘው እሮጌ በምትባል ሥፍራ ላይ ጦርነት ገጥመው የዓፄ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ የነበሩት ፊታውራሪ ገብርዬ ሞቱ።
- ፲፱፻፵፬ ዓ/ም - የአዲስ አበባው ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ተመረቀ፡፡
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - የአሜሪካ ፕሬዚደንት ሊንደን ጆንሰን ጥቁር አሜሪካውያን ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤት ጭቆና ሕገ-ወጥ የሚያደርግ የሰብዓዊ መብት ሕግ አጽድቀው ፈረሙ።
ልደት
ለማስተካከልዕለተ ሞት
ለማስተካከል- ፲፱፻፫ ዓ/ም - የልጅ ኢያሱ ሞግዚት የነበሩትራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው አልፈው በደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
ዋቢ ምንጮች
ለማስተካከል- መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ዕለታዊ የታሪክ ድርጊት - የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያው ፓትረያርክ (፲፱፻፶፩ ዓ/ም)
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |