መጋቢት ፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፹፰ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፸፫ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፸፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፸፯ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ለማስተካከል

  • ፲፰፻፺፪ ዓ/ም - በሩሲያው ንጉሥ ዛር እስክንድር ሣልሳዊ አዲስ አበባ ላይ የተገነባው እና በሩሲያ የቀይ መስቀል ማኅበር ስም የተሠየመው የከተማዋ የመጀመሪያው ሆስፒታል (በኋላ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል) ተመርቆ ተከፈተ።
  • ፲፰፻፺፪ ዓ/ም - ዳግማዊ ምኒልክ በአገሪቱ እየጨመረ የመጣውን ሰካራምነት ለመከላከል በሚል ዓላማ ከውጭ የሚገቡትን መጠጦች የሚያግድ አዋጅ አወጁ።
  • ፲፱፻፹ ዓ/ም - የኤርትራ ነጻነት ግንባር ሠራዊት በአፋበት ግንባር በተሰማራው የ’ናደው እዝ’ ጦር ላይ ከጎንና ከኋላም አስርጎ ሲያጠቃ በኮሎኔል ጌታነህ ኃይሌ የሚመራው የናደው እዝ በከፍተኛ ሽብር ሊሸነፍ ቻለ።

ልደት ለማስተካከል

ዕለተ ሞት ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ