ጥር ፳፭፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፵፭ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፴ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፳፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፳ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች ለማስተካከል

  • ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር በደቡብ አፍሪካ ከተማ፣ ኬፕ ታውን ላይ ‘የለውጥ ነፋስ’ (Wind of Change) በመባል የሚታወቀውን ንግግር አደረጉ። ይህ ታሪካዊ ንግግር የብሪታንያን የቅኝ ገዥነት የታሪክ ምዕራፍ መዘጊያነቱን ያበሠረ ንግግር ነበር።
  • ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - በኡጋንዳ ኢዲ አሚን በተፈነቀሉት ሚልተን ኦቦቴ ምትክ የአገሪቱ መሪ ሆኑ።
  • ፲፱፻፹፪ ዓ/ም የአፓርታይዳዊዋ ደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ደ ክለርክ ለሠላሳ ዓመታት በሕግ ተከልክሎ የነበረውን የአፍሪቃ ብሔራዊ ምክር ቡድን (African National Congress) ሕጋዊ መሆኑንና በወቅቱ በእሥራት ላይ የነበሩትን ኔልሰን ማንዴላ እንደሚፈቱ አስታወቁ።

ልደት ለማስተካከል

ዕለተ ሞት ለማስተካከል

ዋቢ ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ ጳውሎስ ኞኞ፣ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ፣(፲፱፻፹፬ ዓ/ም)ገጽ ፬፻፵፫


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ