ጳውሎስ ኞኞ
ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ ኅዳር 11 ቀን 1926 ዓ.ም ቁልቢ አካባቢ ተወለደው ድሬዳዋ ከተማ አደጉ። በጣም ቆንጆ ስለነበር የልጅነት ስሙ አማረ ይባል፡ ከጊዜ በኋላ ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ስሙ ጳውሎስ ሊባል ችሎአል።
በጣሊያን ወረራ ምክንያት ትምህርታቸውን ከ4ኛ ክፍል በላይ ለመቀጠል አልቻሉም ነበር። ብልህ አዕምሮና የፈጠራ ችሎታ የነበራቸው ሰው ስለነበሩ፤ በልጅነታችው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጣሊያንን ሲገድሉ ወይንም ሲማርኩ ሥዕል በመሣል ያሳዩ ነበር። ጳውሎስ ካላቸው የጽሑፍ ጥማት የተነሳ የ«ድምጽ ጋዜጣ» አዘጋጅ በመሆን የብዕር ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር። ጋዜጦች ላይ ከጽሑፍ አቅራቢነት እስከ አዘጋጅነት ለበርካታ ዓመታት ሠርተዋል። በተለይ «አንድ ጥያቄ አለኝ» በሚለው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አምዳቸው ላይ ብዙ ታዋቂነትን አግኝተዋል። አቶ ጳውሎስ ኞኞ ከ1955 ዓ.ም ጀምሮ ለኢትዮጵያ ስነ ጽሑፍ ዕድገት የነበራቸውን ተሰጥኦ በአግባቡ በሥራ ላይ ያዋሉ እውቅ ጋዜጠኛና ደራሲ ነበሩ።[1] እኚህ ታዋቂ ሰው በተወለዱ በ58 ዓመታቸው ሞቱ።
አቶ ጳውሎስ የጌታችው ሚስቶች በሚል ርዕስ ያሳተሟትን መጽሐፍ፤ «ከታተመችበት ወር አንሥቶ ላንድ ዓመት የመጽሐፌ መብት የግሌ ነው፡ ከአንድ ዓመት በኋል መብቱ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ይሁን፡ ከወሰንኩት ጊዜ በኋላ አሳትሞ ለመሸጥ የፈለገ ሁሉ ከድርሰቴ ሳይቀንስም ሆነ ሳይጨምር ሊያራባው ይችላል። ስሜን ሳይሰርዝ 'አሳታሚውን እገሌ' ብሎ ማንም ኢትዮጵያዊ ከፈለገ እንዲያራባት የደራሲነት መብቴን ልቅቄአለሁ፡ አሳታሚው የግሉን የመግቢያ ሐተታ በስሙ ቢጽፍ እኔም ሆንኩ ወራሼ አንቃወምም።» ብለዋል
የጳውሎስ ኞኞ ድርሰቶች
ለማስተካከልከጋዜጠኝነታቸው ጎን ለጎን በድርሰትና በታሪክ ጸሐፊነታቸውም ፲፱ መጻሕፍት የታተመላቸው ሲሆን ሁለቱ ካረፉ በኋላ የታተሙ ናቸ። ለሕዝብ የሚሆኑ ዕውቀት ተኮር መጻሕፍት በማቅረብ ይታወቁ የነበሩት አቶ ጳውሎስ ኞኞ ካረፉ ከ፳ ዓመታት በኋላ ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ በሀገር ውስጥ የተጻጻፏቸውንና ወደውጭ አገር የላኳቸውን ደብዳቤዎች የሚያሳዩት ሁለት መጻሕፍት በአስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ታትመዋል።[2]
አጫጭር ልብ ወለዶች
ለማስተካከል- ከሴቶቹ አምባ
- የአራዳው ታደሰ
- የጌታቸው ሚስቶች
- ድብልቅልቅ
- የኔዎቹ ገረዶች
ታሪካዊ መጻሕፍት
ለማስተካከልጥቅስ
ለማስተካከልስለጸሐፊነት ባህሪያቸው ሲጽፉ፦ «'ይምሰል አይምሰል የጠይብ እጅ ከከሰል' እንደሚባለው እጄ እንደልማድ ሆኖበት መሞጫጨርን ይወዳል፡ ያን ሟጫራዬን ደግሜ ካነበብኩ ቀድጄ መጣል ነው፤ ይሰለቸኛል፡ እጠለዋለሁ፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ በማርቀቅ የጻፍኳትን እንድትታተም እፈርድባታለሁ። ምናልባት አባጣ ጎባጣ ሆኖ አላስኬድ የሚል ገደላገደል ቢያጋጥማችሁ በደምዳሜ እመር እያላችሁ አላፉት።» [3]