ዲምቱ
በወላይታ ዞን የምትገኝ ከተማ
ዲምቱ ወይም ወላይታ ዲምቱ ከተማ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት፣ በዎላይታ የሚትገኝ ከተማ አስተዳደር ናት። ከተማዋ ከዚህ ቀደም በነበረው አወቃቀር በዳሞት ወይዴ ወረዳ ስር የነበረች ቢሆንም፣ አሁን ግን በድጉና ፋንጎ ወረዳ ስር ትገኛለች።[1]
ዲምቱ | |
ከተማ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት |
ዞን | ዎላይታ |
ወረዳ | ድጉና ፋንጎ |
ካንቲባ | ኢዩኤል ሞላ |
ከፍታ | 1,400 ሜ. |
ታሪክ
ለማስተካከልዴቪድ ቡክሰን የተባለ ጻሓፊ፥ ዲምቱ በብላቴ ወንዝ አካባቢ የሚገኝ የገበያ ስም እንደሆነ ጽፎ ነበር።[2] አንዳንድ አፈታሪኮች እንደምጠቁሙት ከሆነ ገበያው ስያሜውን ያገኘው ከከተማዋ የሚወጣ ትንሽ ንጹህ ወንዝ ከብላቴ ወንዝ ጋር በሚገናኙበት ገበያው ይቆም ስለነበረ ነው። ይህን መገናኘት በወላይትኛ ዳንቷ እያሉ ይጠሩትም ነበር፤ መገናኛ ማለት ነውና። ከጊዜና ከቃሉ አጠራር ዘዬ ጋር ተያይዞ የአሁኑን ስያሜ ይዞ ለከተማውም ስም ሆኖ አረፈው ይባላል። ዲምቱ በወላይታ ውስጥ ከሶዶ ቀጥሎ እጅግ ረጅም ዕድሜ ያስቆጠረች ከተማ ናት። ከተማዋ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ 333 ኪሎ ሜትር ርቃ የሚትገኝ ሲሆን፥ ከዞኑ ዋና ከተማ ሶዶ ደግሞ በ68 ኪሎ ሜትር ርቀት በስተምሥራቅ ትገኛለች። ከተማዋ በስተምሥራቅ በብላቴ ወንዝ የሚትዋሰን ሲሆን ውንዙ ከሲዳማ ክልል እና ከኦሮሚያ ክልል በተመሳሳይ ሁኔታ ያገናኛታል።
ዋቢ
ለማስተካከል- ^ "Admirative Map of SNNPR". በ6 October 2020 የተወሰደ.
- ^ David, Buxton. David Roden Buxton. David Roden Buxton. pp. 66.