ወላይትኛ
ወላይትኛ በኢትዮጵያ በተጠቃሚ ብዛት በ4ኛነት የሚመደብና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው የሚነገር ቋንቋ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የሌሎቹ ተቀራራቢ ቋንቋዎች ምንጭ ነው። ወላይትኛ ከሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በፊት የመጀመሪያው የላቲን ፊደል መጽኃፍ ቅዱስ ታትሞበታል። ከወላይትኛ ጋር ዝምድና ያላቸው ሌሎች ቋንቋዎች ጋሞ-ጎፋ-ዳውሮ እና ኩሎና ኮንታ ናቸው። ባሁኑ ጊዜ በሥልጣን ላይ ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት እነኚህን ተቀራራቢ ቋንቋዎች ነገር ግን 25% ትርጓሜዎቻቸው እርስ በርሳቸው በፍጹም የማይገናናኙትን <ዎጋጎዳ> በማለት አዲስ ስያሜ በመስጠት የ1ኛ ደረጃ መማሪያ መጽሃፍ አዘጋጀ። ይሁን እንጂ በተለይ በወላይታ ተወላጆች ዘንድ ኃይለኛ ቁጣን አስነስቶ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን በማጣታቸው ጉዳዩ የዓለምን ትኩረት ስቦ ነበር። ለምሣሌ ያህል፡ <ኦታ> ማለት በወላይትኛ ሥራ ማለት ሲሆን በጎሙኛ ግን ግብረ ሥጋንኙነት የሚል ትርጓሜ ስላለው ለኅብረተሰቡ ያልተለመደና እጅግ አስነዋሪ ቃል ነው። በአንጻሩ ግን አብዛኛው ቃል ቢመሳሰልም በመጽኃፍ ደረጃ ታትሞ ለልጆች ትምህርት እንዲውል ገዢው መንግሥት በቂ ጥናት ስላላደረገ በቂ ግንዛቤ አልነበረውም። በተመሳሳይ ሁኔታ የዎላይታ ብሄራዊ ክልል ጥያቄ የህዝብ ጥያቄ ሆኖ የዞን አመራሮችና ጥቂት ግለሰቦች ነዉ በማለት ወላይተኛ ተናጋሪዎች መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ አፈና ደርሶባቸዋል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
በዉስጡ ብዙ ቋንቋውን