የ1986 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ
የ1986 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፲፫ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የነበረ ሲሆን ውድድሩ ከግንቦት ፳፫ እስከ ሰኔ ፳፪ ቀን ፲፱፻፸፰ ዓ.ም. በሜክሲኮ ተካሄዷል።
የ1986 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ |
|
---|---|
ይፋዊ ምልክት
|
|
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ሜክሲኮ |
ቀናት | ከግንቦት ፳፫ እስከ ሰኔ ፳፪ ቀን |
ቡድኖች | ፳፬ (ከ፭ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲፪ ስታዲየሞች (በ፱ ከተማዎች) |
ውጤት | |
አሸናፊ | አርጀንቲና (፪ኛው ድል) |
ሁለተኛ | ምዕራብ ጀርመን |
ሦስተኛ | ፈረንሣይ |
አራተኛ | ቤልጅግ |
እስታቲስቲክስ | |
የጨዋታዎች ብዛት | ፶፪ |
የጎሎች ብዛት | ፻፴፪ |
የተመልካች ቁጥር | 2,393,031 |
ኮከብ ግብ አግቢ(ዎች) | ጌሪ ላይነከር ፮ ጎሎች |
ኮከብ ተጫዋች | ዲየጎ ማራዶና |
← 1982 እ.ኤ.አ. 1990 እ.ኤ.አ. → |
ፊፋ በመጀመሪያ ኮሎምቢያ ውድድሩን እንድታዘጋጅ የመረጣት ቢሆንም በኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ወደ ሜክሲኮ ተላልፏል። ውድድሩን ያሸነፈው አርጀንቲና ሲሆን የማራዶና ታዋቂ የእግዚአብሔር እጅ ጎልም በዚሁ ውድድር ላይ በእንግሊዝ ቡድን ላይ ነው የገባው።