የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች

ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የባህል ሙዚቃ መሣሪያዎች አሉ። እነዚህም መሣሪያዎች የጅማት፣ የትንፋሽና የምት ተብለው ወደ ሶስት ይከፈላሉ።

የክር ሙዚቃ መሣሪያዎች

ለማስተካከል

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በንዝረት ነው።

  • በገና፡ መንፈሳዊ ዜማዎችን ለማዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ክራር፡ ይህ የጅማት የሙዚቃ መሣሪያ ለአያሌ ዓመታት ለደስታ፣ ለትካዜ፣ ለፍቅርና ለቀረርቶ ስንጠቀምበት የቆየ መሣሪያ ነው።
  • መሰንቆ (ማሲንቆ)፡ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚገኝ ጥንታዊ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ዲታ፡ በሲዳሞ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።
  • ዱል፡ በጋምቤላ የሚገኝ የጅማት መሣሪያ ነው።

የትንፋሽ ሙዚቃ መሣሪያዎች

ለማስተካከል

እነዚህ መሣሪያዎች ድምጽ የሚሰጡት በትንፋሽ ኃይል ነው።

  • ዋሽንት፡ አብዛኛውን ጊዜ እረኞች በሀገር ቤት ይገለገሉበታል። በተጨማሪም በመድረክ ላይ ለክራርና ለመሰንቆ ቅኝት በመስጠትና ዜማን በማጀብ ያገለግላል።
  • አምቢልታ፡ ሶስት ዓይነት አመቢልታዎች አሉ። ስማቸውም ኡፍንአውራ እና የማ ነው። በኢትዮጵያ ለክብረ በዓልና ወደ ጦር ሜዳ ለሚሄድ ሰልፈኛ የሚነፋ አድማቂ መሣሪያ ነው።
  • መለከት፡ ቀደም ባለው ጊዜ ሰዎች ተሰብስበው የመንግሥት አዋጅ እንዲሰሙ ትዕዛዝን መስጫ መሣሪያ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ነው።
  • ድንኬ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር በወላይታ አካባቢ ለአስከሬን ማጀቢያነት የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ፖረሬሳ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ለዘፈን ማጀቢያ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ሁራ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር ያሉ ጎሳዎች የሚጠቀሙበት የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ሁልዱዱዋ፡ በሲዳሞ ክፍለ ሀገር የቀብር ሥነ ሥርዓት ለመግለጽ የሚነፋ መሣሪያ ነው።
  • ጨቻ ዝዬ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ውዝዋዜ ለማድመቅ የሚያገለግል የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ዛክ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ሸመቶ፡ በከፋ ክፍለ ሀገር የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • ፋንፋ፡ በከፋ ክፍለ ሀገርና በጋሞጎፋ /ኮንሶ/ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • አዋዛ፡ በወለጋ ክፍለ ሀገር በአሶሳ አካባቢ የሚገኝ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።

የምት ሙዚቃ መሣሪያዎች

ለማስተካከል
  • ከበሮ፡ ለዘፈን ማድመቂያና ለሠርግ እንዲሁም ለቤተ ክርስቲያን ዝማሬ ቀሳውስት በሽብሸባ ጊዜ የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • አታሞ፡ ለሙዚቃና ለጭፈራ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ነጋሪት፡ በሰልፍ ጊዜ የሚጎሰም የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • መቋሚያ፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ከከበሮው ስልት ጋር በተዛመደ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • ፀናፅል፡ ለመንፈሳዊ ዝማሬ ቀሳውስት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ነው።
  • ቅል፡ ቅል በውስጡ ጠጠሮች ወይም ፍሬዎች ተጨምረውበት ለዘፈን ማድመቂያ ያገለግላል።
  • ቻንቻ፡ በጋሞጎፋ ክፍለ ሀገር በጭፈራ ጊዜ በወገብ ላይ የሚታሰር አዳማቂ መሣሪያ ነው።
  • ካመባ፡ ከሸክላ የተሠራ በደቡብና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ መሣሪያ ነው።
  • ቃጭል፡ አብዛኛውን ጊዜ ለመንፈሳዊ ዜማ የሚያገለግል መሣሪያ ነው።
  • ቶሞ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ እውቅና ተወዳጅ የሆነ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። በተጨማሪም በኬንያኡጋንዳታንዛኒያናይጄሪያሱዳንዛየርም በዚህ መሣሪያ እንደሚጠቀሙ ታውቋል።
  • ጋሬ፡ በጋምቤላ ብሔረሰብ ውስጥ በእግር ላይ ታስሮ ጭፈራን የሚያደምቅ የሙዚቃ መሣሪያ ነው።
  • የግመል ቃጭል፡ ይህ መሣሪያ በተለይ ከእንጨት የሚሠራ ሆኖ ሙዚቃን ለማጀብ የሚጠቅም መሣሪያ ነው።

ተዛማጅ መጣጥፎች

ለማስተካከል