ክራር ባለ አምስት ወይም ስድስት ክር (ጅማት) የሙዚቃ መሳሪያ ነው።

ክራር

አሰራር ለማስተካከል

==ታሪክ == የበገና ዓይነት የዜማ ዕቃ ነው ። የዘመናችን ክራር አምስት ወይም ስድስት የጅማት አውታሮች አሉት ። ክራርን በበገና ዓይን ካላየነው በቀር በክራር ሲዘመር እንደ ነበር ክራር የመዝሙር መሣሪያ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙር መሳሪያነት ጠቅሶት አናገኝም ። በስም ግን ጠርቶት ይገኛል ። ናቡከደነጾር ጣዖቱን ካሳጀበባቸው መሣሪያዎች አንዱ ክራር እንደ እንደ ነበረ በትንቢተ ዳንኤል ተጠቅሶ እናነባለን ። 3 ፥ 5-7 ። ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ልሳን ሲናገር ሕይወት የሌላቸው መሣሪያዎች ሲቃኙ እንደ ቅኝታቸው ስሜት የሚሰጥ ድምጽ ይሰጣሉ ። እንዴት እናንተ በልሳን እንናገራለን እያላችሁ ትርጉም የለሽ ነገር ትናገራላችሁ ብሎ የቆሮንቶስን ቤተ ክርስቲያን ግብዞች ባስተማረበት ክፍል ለምሳሌ ከጠቀሳቸው መሣሪያዎች ክራርና ዋሽንት ይገኙበታል ። 1ቆሮ 10 ፥7 ። በተጨማሪም ክራር በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን /የአሁኑን ዘመን አይጨምርም/ የጐላ የመዝሙር ቦታ ተሰጥቶት አልተነበበም ። ይሁን እንጂ በክራር መዘመሩ በደል አይደለም ። ቤተ ክርስቲያን ግን ባትለየውም እውቅና አልሰጠችውም ። በአሜሪካ ያሉት አባቶች ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስም ሆነ በኢትዮጵያ ያሉት አባቶች ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ በውሳኔው ውስጥ በተራ ቍጥር አልጠቀሰውም

ሙዚቃዊ ባህር ለማስተካከል

ክራር ከአንድ ሜጀር እስኬል ወደሌላ ሜጀር እስኬል ለመቃኘት በቀላሉ በአንድ ክር መሻገር ይቻላል ምሳሌ 1፦C D E F G A B C ይህ ማለት ዲያቶኒክ እስኬል ሲሆን 4 እና 7ን በማስወጣት ፔንታቶኒክ እስኬልን በመገንባት C D E G A C or DO RE MI SOL LA DO ሁለቱም ቋንቋ ነዉ የሚለያቸዉ C D E G A C ማለት በእንግሊዘኛ ሲሆን DO RE MI SOL LA DO ማለት በጣሊያንኛ ነዉ ስለዚህ ክራርን ስንቃኝ ከC ትዝታ ወደ G ትዝታ ሜጀር ለመሻገር 1 ክር ከC ወደ D 2 ክር ከC ወደ A 3 ክር ከA ወደ E 4 ክር ከC ወደ B 5 ክር ይህ ማለት በቀላሉ 12 ሜጀር እስኬሎች አሉ እነዚህ እስኬሎች አንድ አንድ ክር ፈርስቱን በግማሽ በማዉረድ ይህ ማለት C መነሻችን ከሆነ ወደ G ለመሄድ Cን በግማሽ ድምፅ በማዉረድ Gን ፈርስት ማድረግ እንችላለን ማለት ነዉ በዚህ መሰረት C G D A E B F# C# A" E" B"Fን እናገኛለን ማለት ነዉ ወደነበርንበት ለመመለስ ሶስተኛዉን ድምፅ በግማሽ በማዉጣት ከC ወደ F ለመቃኘት የCን ሶስተኛዉን Eን በግማሽ በማዉጣት ወደ F እንሻገራለን ማለት ነዉ።