በገና
በገና በተወጠሩ ክሮች የሚሰራ የኢትዮጵያ የሙዚቃ መሳሪያ ነው። በገና ሌላው ስሙ በግዕዝ እንዚራ ተብሎ ይጠራል። ቁመቱ ረዘም ገበታው ሰፋ ያለ ከ 90 ሳንቲ ሜትር እስከ 140 ሳንቲ ሜትር ርዝመት ያለውና 10 ጅማቶች (አውታሮች) ያሉት ጥንታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የመንፈሳዊ መሳርያ ነው።
አሰራር
ለማስተካከልሳጥኑ፣ ምሰሶዎቹ፣ ብርኩማውና ቀምበሩ ከንጨት የሚሰሩ ናቸው። አውታሮቹም ከጅማት ይሰራሉ። ሳጥኑ በበግ ወይም በከብት ቆዳ ይሸፈናል። ድዝና ጥዝ እንዲል 10 ቁርጥራጭ ቆዳዎች በብርኩማውና በአውታሮቹ መካከል ይስተካከላሉ። ቀምበሩ የእግዚአብሔር ምሳሌ (ምልክት) ነው። ምሰሶዎቹ በስተቀኝ የቅዱስ ሚካኢል በስተግራ የቅዱስ ገብርኢል ምሳሌዎች (ምልክቶች) ናቸው። ጅማቶቹ (አስሩ አውታሮች) የአስርቱ ቃላት ኦሪት ምሳሌ (ምልክት) ናቸው። የድምጽ ሳጥኑ (ገበታው) የእመቤታችን ምሳሌ ነው። ብርኩማው የሙሴ አስርቱን ትዕዛዛት የተቀበለበት የደብረ ሲና ምሳሌ ነው።
ታሪክ
ለማስተካከልበገና ወደ ኢትዮጵያ የገባው ከክርስቶስ ልደት በፊት በቀደምት የኢትዮጵያ ነገስታት በኩል ሲሆን በቅርብም ከነበሩ ነገስታት አጼ ምኒልክና አጼ ቴዎድሮስ በገና ይደረድሩ እንደ ነበር ይነገራል።
ዜማዊ ባህርዩ
ለማስተካከልየበገና ዜማ በአብዛኛው ለፈጣሪያችን ምስጋና ፀሎት ለማቅረብና ባጫጭር ዜማዎች የዚህ አለም አላፊነትን የሚናገር ሰዎችን ለበጎ ሥራ የሚቀሰቅስ ወደ ንስሐ የሚጠራ ለመንፈሳዊ አገልግሎት የሚጠቅም ነው።
|
|
ይሄን ፋይል ማጫወት ካስቸገርዎት የሚዲያ ማጫወት እርዳታን ይዩ። |
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |