የኢትዮጵያ ካርታ 1690
ስለ ካርታው ታሪክና ትችት
ለማስተካከልምናልባትም እስካሁን ድረስ ያሉ ከተሞችን፣ ተራሮችንና ወንዞችን በትክክል በማስቀመጥ ወደር የሌለው ካርታ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ካርታው የተዘጋጀው በቬኒስ ካርታ ሰሪ ቪቸንዞ ኮርኔሊ (Vincenzo Maria Coronelli (August 16, 1650 - December 9, 1718) ) በ1690 ነበር። ይህ ሰው የመጀመሪያውን የጂኦግራፊ ማህበር Accademia Cosmografica degli Argonauti, በ1680 የመሰረት ነበር። ለካርታው ዋቢ የሆኑት በ1600ወቹ ኢትዮጵያን የጎበኙት የፖርቱጋል ተጓዦች፣ ማኑኤል ደ አልሜዳ፣ አልፎንሶ ሜንዴዝ፣ ፔድሮ ፔዝና ጆርሞ ሎቦ ናቸው።
- Tsana = ጣና ሃይቅ - ጣናና ደምቢያ የካርታው ዋና ትኩረት የሆኑበት ምክንያት በዘመኑ የኢትዮጵያ ነገስታ በአካባባቢው ዋና ከተሞችን ይገነቡ ስለነበር ነው። ደንከዝ፣ ጉዛራ፣ ጎርጎራ እና ጎንደር ይጠቀሳሉ።
- ከሰሜኑ የቀይ ባህር ወደብ Derbeta ጀምሮ አሁን ደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙት Sugame, Bahargamo and Gumar በግልጽ ይታያሉ። የአስመራ ከተማም በታሪክና በዚህ ካርታ ላይ ብቅ ይላል።
- Axum አክሱም , Asmara አስመራ, Gojiam ጎጃም, di Cafate ጋፋት, di Ganz ገንዝ , Bahargamo ብሄር ጋሞ, Walkajit ወልቃይት, Gorgoraጎርጎራ, Samen ሰሜን, Lalibela ላሊበላ, Shewa ሸዋ ,Mugar ሙገር ,di Dembea ደምቢያ Tigre ትግራይ, di Amhara ደቡብ ወሎ, Ifat ይፋት, Guraghe ጉራጌ, Damot ዳሞት, Balli ባሌ, Dawaro ዳዋሮ, Sugamo ሲዳሞ, Angot አንጎት, Bagemder ጎንደር and Midrabahr ምድር ባህር (ኤርትራ) በሚገባ ካራው ላይ ይስተዋላሉ። የንጉሱ መቀመጫ ይጠቀስ እንጂ በርግጥ በጊዜው የአገሪቱ ዋና ከተማ ጎንደር ከተማ ካርታው ላይ አልሰፈረም።
ማውስወን ካርታው ላይ በማንሳፋፍ የአማርኛ መረጃ ያገኛሉ
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ Coronelli, Vincenzo, 1650-1718. “Abissinia, doue sono le Fonti del Nilo. . . .” Copperplate map, with added color, 43 x 58 cm. From Coronelli’s Atlante Veneto . . . (Venice, 1690 or 1695). [Historic Maps Collection]