?የምድር እምቧይ
የምድር እምቧይ
የምድር እምቧይ
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: አትክልት (Plantae)
ክፍለመደብ: የዱባ ክፍለመደብ
አስተኔ: ዱባ Cucurbitaceae
ወገን: የኪያር ወገን Cucumis
ዝርያ: የምድር እምቧይ (C. prophetarum)

የምድር እምቧይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ለማስተካከል

የዚህ ኪያር ፍሬው በጣም መርዛም ነው አይበላም።

የምድር እምቧይ በውነት እምቧይ አይደለም፤ የኪያር ዘመድ ነው።

ሮማይስጥ ስሙ Cucumis prophetarum ማለት «የነቢያት ኪያር» ሲሆን፣ ይህም ከአረብኛው «የኒቢዩ ኪያር» ወይም «የውሻዎች ኪያር» ከመባሉ ነው።

ሌላ ተመሳሳይ የኪያር ወገን ዝርያ Cucumis ficifolius ደግሞ «የምድር እምቧይ» ተብሏል።

ከዚህም በላይ የምድር እምቧይ ቢጫው ፍሬ እንደ ሌላ ዱባ ዝርያ የበረሃ ቅል Citrullus colocynthis ትንሽ ይመስላል፤ እሱም (Citrullus colocynthus) ደግሞ አንዳንዴ «የምድር እምቧይ» ተብሏል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ለማስተካከል

በመስክ ይታያል። በከፊል ደረቅ አየር ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም

ለማስተካከል

ፍሬው ለልጆች ኳስ ተጠቅሟል እንጂ መርዛም ስለ ሆነ አይበላም።[1]

በአንድ ጥናት ዘንድ፣ ሥሩ (C. ficifolius) የተለያዩ ጥቅሞች እንዳሉት ተዘገበ። ሥሩን መብላት ለእባብ ነከስ፣ ወይም ለ«ሞኝ ባገኝ» (አበባ ሰንጋ)። ሥሩን ጭማቂውንም መኘካት ለሆድ ቁርጠት ወይም ለትኩሳት («ምች»)። ሥሩ ተድቅቆ እንደ ለጥፍ ለ«ቁስል መርዝ» (የቁስል ልክፈት)። ሥሩ በቅቤ እንድ ለጥፍ ለችፌ። ሥሩም ከአንዳንድ ሌሎች ተክሎች ጋር ሌሎችንም ጥቅሞች አሉት።[2]

በተጨማሪ ጥናት፣ የሥሩ (C. ficifolius) መኘካት ደግሞ ለቁርባአኖሬክሲያ፣ ለወላድ ምጥ ያከማል፤ የሥሩም ዱቄት በማርማጅራት ገትር ይበላል፣ በጤፍ ቂጣ ለውሻ በሽታ ይበላል፤ በ[[ወተት] ወይም ኑግወፍ በሽታ በጥዋት ይጠጣል፤ ወይም ለነስር የሥሩ ጭማቂ ወደ አፍንጫ ማስገባት ነው።[3]

እንደገና በሌላ ጥናት፣ የመላው C. ficifolius ተክል መረቅ ትልን ለማስወጣት፣ ወይም የከብቶች ተቅማጥ ለማከም፣ ለመጠጣት ይሰጣል።[4]

  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE Archived ጁላይ 31, 2017 at the Wayback Machine March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
  4. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች