ኑግሮማይስጥ Guizotia abyssinica በመባል የታወቀው የእህል ዘር የሚሰጥ ተክል ዝርያ ነው። ኑግ ዩናይትድ አስቴትስ ውሱጥ ተወዳጅ የወፍ ምግብ ነው። ይህን የዘይት እህል በብዛት የሚያመርቱ ኣገሮች ኢትዮጵያሕንድ ናቸው ይባላል፣ ሌሎችም አሉ።

ኑግ አበባ

ወፎች ስለሚወድዱት ብዙ አገሮችም ያስገቡታል። ዘሩ ወደ ሌላ አገር ሳይገባ ግን የአረም ዘሮች ስላሉበት ስንኩል እንዳይሆኑ ለ15 ደቂቃ በከፍተኛ ሙቀት እንዲቆይ ይገደዳል።

በደቡብ ሕንድ ምግብ አበሳሰል በወጥ ወይም ስጎ ውስጥ ይጨመራል።

የኑግ ዘይት፣ ቅባኑግ ደግሞ ያስገባሉ፤ ለአበሳሰል በወይራ ዘይት ፈንታ ሊጠቀሙ ይችላሉ፣ ወይም ሳሙና፣ ቀለም መቀብያ ለማዘጋጀት ለኢንዱስትሪዎች ይጠቀማል። በተለይ በኢትዮጵያ ቅባኑግን ከማውጣት የተረፈው የዘሩ እንጐቻ ለከብት መኖ ይሰጣል።

በኢትዮጵያ በተቆለለና በደቀቀ ኑግ ውጥ በስኳርና በውሃ ጉንፋን በማከም ይጠቀማሉ። የደቀቀ ኑግና ተልባ ተዋህዶ ቆዳን በመቀባት ለቆዳ ውበትና ጤና ይጠቅማል። ኑግና ጥቁርአዝሙድ ተፈጭቶ ከዝንጅብል ጋር በማዋሃድ በጁስ መልክ በሁለትኩባያ ውሃ ይፈጭና በማጥለያ አጥልሎ ጭማቂውን በቀን አንዴ በመጠጣት የደምግፊትን፣የስኳርበሽታንእንዲሁም የሆድ ቦርጭን ለመቀነስ ይጠቅማል። ኑግ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው። እንዲሁም የኑግና የመተሬ ዘር ተዋህዶ ለኮሶ በሽታ ይሰጣል። ቁንጭር (ሌይሽመናይሲስ) ለማከም የኑግ፣ የነጭ ሽንኩርት ልጥና የኣዞ ሓረግ ቅጠል ተደቆ በለጥፍ ትንሽ ሙቅ ተደርጎ ይቀባል።[1]


  1. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም