የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች
(ከየማይክሮኔዝያ ፌዴሬትድ ስቴትስ የተዛወረ)
የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች በሰላማዊ ውቅያኖስ የሚገኝ የደሴቶች አገር ነው። ዋና ከተማው ፓሊኪር ነው።
የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: "Patriots of Micronesia" |
||||||
ዋና ከተማ | ፓሊኪር | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ | |||||
መንግሥት {{{ ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
ፒተር ክርስቲያን ዮሲዎ ጆርጅ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
702 (177ኛ) |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት |
102,800 [1] (184ኛ) |
|||||
ገንዘብ | የአሜሪካ ዶላር | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +10 እስከ +11 | |||||
የስልክ መግቢያ | +691 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .fm |
ዋናው ኢንዱስትሪ ከውቅያኖስ አሣ በተለይም ጦን ማጥመድ ነው። የመቆያ ግብርና ብቻ አለ፤ ዋና ምርቶቹም ኮኮነት ዘምባባ፣ ሙዝ፣ አሬካ ዘምባባ፣ ካሳቫ፣ ስኳር ድንች ናቸው። እንግሊዝኛ የሥራ ቋንቋና መደበኛው ቋንቋ ነው፤ የተለያዩ የልዩ ልዩ ደሴቶች ኗሪ ቋንቋዎች አሉ።
ታሪክ
ለማስተካከልዙሪያው ለ1100 እስከ 1600 ዓም ግድም ድረስ የሳውደዩር መንግሥት ተባለ፤ በዚያም ጊዜ ኢሶከለከል ለተባለ አሸናፊ እንደ ወደቀ በአፈ ታሪክ ይባላል። የኢሶከለከል ሥርወ መንግሥት እስከ 1878 ዓም ድረስ ቆየ፤ ከዚያ በኋላ የእስፓንያ ቅኝ ግዛት ሆነ። አውሮጳዊ ተጓዦች ግን ከ1522 ዓም ጀምሮ በመርከብ ይጎበኙ ነበር። የእስፓንያ ቅኝ ግዛት መሆኑ ከ1878 እስከ 1891 ዓም ቆየ፣ በ1891 ዓም ለጀርመን መንግሥት ተሸጠ። በ1906 ዓም አንደኛው የዓለም ጦርነት ሲጀመር ጃፓን ደሴቶቹን ከጀርመን ያዛቸው፤ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ግን በ1936 ዓም አሜሪካ ከጃፓን ያዛቸው። ከጦርነቱ በኋላ በይፋ የተመድ አደራ ተብሎ በአሜሪካ አስተዳደር ስር እስከ 1979 ዓም ድረስ ቆየ።