ውክፔዲያ:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ

የአዲስ መጣጥፍ ሰም ሲያወጡ ይህን መጣጥፍ እንዲያዩ ይመከራል።

እንደ አለም ጠንካራ ዞን ኦሮሚያ ልዩ ዞን ናት

ነጠላ ቃል ይጠቀሙEdit

ለምሳሌ ስለ መኪና አዲስ ገጽ ሊጨምሩ ከሆነ አርዕስቱን መኪናዎች ሳይሆን መኪና ብለው ይሰይሙት። ለመደቦች ግን የተለየ መመሪያ አለ።

የአማርኛ ቃል ይጠቀሙEdit

ስለ orange የሚጽፉ ከሆነ አርዕስቱን ብርቱካን ይበሉት፤ በመጣጥፉ መጀመሪያው ዐረፍተ ነገር ላይ ግን በኩር (አሪጅናሉ) ቋንቋ ካለ በቅንፍ ይጻፉት። ለምሳሌ፦

ሴንት ጆንስ (እንግሊዘኛSt. Johns) በአሪዞና የሚገኝ ከተማ ነው።
ኮኝስኮቮላ (ፖሎኝኛKońskowola) በደቡባዊ ምስራቅ ፖላንድ የሚገኝ ሰፈር ነው።

ከምጻረ ቃሎች ዝርዝር ቃሎችን ይምረጡEdit

ከምጻረ ቃሎች ዝርዝር ቃሎችን ይምረጡ ግን ከምጻረ ቃሉ ወደዝርዝሩ መያያዣ ይስሩ። ለምሳሌ፦ ኢዜአ ከማለት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ይበሉት።

የዘመን አቆጣጠር ሥርዓትEdit

ለስፖርት-ነክ ዓመታት የእግር ኳስ ንዑስ ክፍልን ከስር ይዩ።

የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ቢጠቀሙ ይመረጣል። ነገር ግን ለአሁኑ ጊዜ ዓመታት የሚጻፉት እንደ አቅራቢው ምርጫ ነው። የሚሻ ግን መቆጠሪያው በምን አይነት እንደሆነ በግልጽ ለመግለጽ ነው።

 • በኢትዮጵያ መቁጠሪያና በግሬጎርያን መካከል የ7 ወይም 8 አመት ልዩነት አለ። ስለዚህ ፦

1998 አመተ ምህረት = 2005 ወይም 2006 እ.ኤ.ኣ.።

ከዚያ ደግሞ የአውሮፓ አቆጣጠር አንዳንዴ "ዓመተ ምህረት' ሊባል ይችላል። ስለዚህ፦

"(ዓ.ም.)" ለኢትዮጵያ ዓመታት
"(እ.ኤ.አ.)" ለግሪጎርያን ብቻ ቢጠቀም ጥሩ ነው።

ወራት ደግሞ የኢትዮጵያ ወይም የግሪጎርያን ሊሆኑ ይችላሉ።

 • እንደ ዓመታት አይነት ተመሳሳይ ይሁኑ። ምሳሌ፦
December 26, 2005 እ.ኤ.ኣ.
-ወይም-
ታኅሣሥ 18 ቀን 1998 ዓ.ም.
 • በቀጥታ ወሮችን ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ የሚያስለውጥ መለጠፊያ ዘዴ አለ።

በተጨማሪ ለመረዳት ውክፔዲያ:የቀን መለወጫ ይዩ።

የቦታ ስም አጻጻፍEdit

ለአርዕስት፦

 • የሀገር ስም ከሆነ በቀላሉ ወይም በሙሉ ስሙን መጻፍ ይቻላል። ከሌላኛው ግን መያያዣ መሥራት ጥሩ ነው።

ለምሳሌ፦ ኢትዮጵያ የሚል መጣጥፍ ካለ፣ ከየኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወደ ኢትዮጵያ መያያዣ መሥራት ያሻል።

 • የክፍለ ሀገር ስም ከሆነ - ስሙ ከዚያም ነጠላ ሠረዝ (፣) እና አንድ ባዶ ሕዋእ ቦታ (space) እና የሀገሩ ስም

ምሳሌዎች፦

 1. አፓቼ ካውንቲ፣ አሪዞና
 2. ፓሪስ፣ ፈረንሣይ
 3. ሀደሌኤላ፣ ኢትዮጵያ

የትምህርት ቤቶች ስም አጻጻፍEdit

የትምህርት ቤቶችን ሙሉ ስም ይጠቀሙ። ያስታውሱ፥ በመጀመሪያው መስመር ላይ በኦሪጂናሉ ቋንቋ ይጻፉ።

ምሳሌዎች፦

 • Arizona State University ወደ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርስቲ
 • Massachusettes Institue of Technology ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት
 • Northern Arizona University ሰሜን አሪዞና ዩኒቨርስቲ
 • University of Maryland ሜሪላንድ ዩኒቨርስቲ

የአውሮፕላን ማረፈያ ሰም አጻጻፍEdit

የአውሮፕላን ማረፊያ ስም ሲጽፉ በተቻለ መጠን ሙሉ ስሙን ይጻፉ። ምሳሌዎች፦

 • ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፈያ
 • ዋሽንግተን ሮናልድ ሬገን ብሔራዊ አውሮፕላን ማረፊያ

የፊልም አርዕስት አጻጻፍEdit

የፊልም አርዕስት ሲጽፉ፦

 • አንድ ከሆነ ስሙን ብቻ ይበቃል
 • ተከታታይ ወይም ከአንድ በላይ ፊልም በአንድ አርዕስት ካለ የተሰራበትን ዓ.ም. ይጨምሩ (የዘመን አቆጣጠር ሥርዐትን ይዩ)
 • በስሙ መጽሐፍ ወይም ሌላ ነገር ካለ (ፊልም) ይጨምሩ - ምሳሌ፦ ታይታኒክ (ፊልም)

የሰው ስም አጻጻፍEdit

አርዕስቱ የሰው ስም ከሆነ "ዶ/ር"፥ "አቶ"፥ "ክቡር"፥ "ወ/ሮ" ፥ ወዘተ አይጨምሩ። በመጣጥፉ የመጀመሪያ መስመር ግን ቢጨምሩ ያሻል። ለንጉሦች ደግሞ "ዓፄ"፥ "ንጉሥ"፥ "ንጉሠ ነገሥት"፥ ወዘተ መንታ መንገድ ለመፍታት ካልሆነ በስተቀር አይጨምሩ።

[[ውክፔዲያ:|መሀመድ ሀከና ሱግኔ]]

እግር ኳስEdit

ዓመታትEdit

ለእግር ኳስ ውድድሮች፣ የሚካሄዱበት ዓመት በይፋ አርዕስታቸው ስለሚጠቃቀል ከግሬጎርያን ወደ የኢትዮጵያ አቆጣጠር ወይም ከኢትዮጵያ ወደ ግሬጎርያን አይለውጡ። ለምሳሌ፦

የቡድኖችና ክለቦች አሰያየምEdit

F.C. «እግር ኳስ ክለብ» በማለት ይተርጉሙ። ለምሳሌ፦