ውክፔዲያ:መንታ መንገድ
በውክፔድያ አንዳንድ መጣጥፍ መንታ መንገድ ይባላል። አንድ ስያሜ ወይም አርዕስት ከአንድ ጉዳይ በላይ ሊያመልከት ሲችል ነው። መንታ መንገድ አንባቢዎች የፈለጉትን መጣጥፍ ቶሎ ለማግኘት ኢንዲረዳቸው ነው።
የመንታ መንገድ ስርዓት እንዲህ እንዲመች ነው። ለምሳሌ፦ ብርቱካን የሚለው ገጽ መንታ መንገድ ነው። በዚያ እንዲህ እናገኛለን፦
«ብርቱካን የተለያዩት ፍች ሊሆነው ይችላል፦
ስም
ለማስተካከል- ብርቱካን ሚዴቅሳ፦ ኢትዮጵያዊት ፖለቲከኛ
- ብርቱካን ዱባለ፦ ኢትዮጵያዊ ድምጻዊት»
መንታ መንገድ ሲያስፈልግ ሊፈጠር ይቻላል። ይህን ለማድረግ በገጹ ላይ {{መንታ}} መልጠፍ ያስፈልጋል። ይህ መለጠፊያ እንዲህ ያለውን ምልክት ያደርጋል፦
ከዚህ በላይ የሚታየው ምልክት በገጹ ላይ ሲኖር፣ ገጹ መንታ መንገድ መሆኑ ደግሞ ለሎሌ (BOT) ይታወቃል።