ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 19
ኅዳር ፲፱
- ፲፰፻፴፮ ዓ.ም. በሐዋይ ደሴቶች የነጻነት ዕለት ነው። የብሪታንያ እና የፈረንሳይ መንግሥታት የሐዋይን ደሴቶች ንጉዛት (ንጉሣዊ + ግዛት)ሉዐላዊነት አወቁ፣ አከበሩ።
- ፲፰፻፵፭ ዓ.ም. - የደጅ አዝማች ካሣ (በኋላ ዓፄ ቴዎድሮስ)ሠራዊትና የጎጃሙ የደጅ አዝማች ጎሹ ተከታዮች ጉራምባ ላይ ተዋግተው ድሉ የደጅ አዝማች ካሣ ሆነ። ደጅ አዝማች ጎሹም በነፍጥ ተመተው ሞቱ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ.ም. የፖርቱጋል ቅኝ ግዛት የነበረችው ምሥራቅ ጢሞር፣ ገዥዋ ስትተዋት የራሷን ነጻነት አወጀች። ከዘጠኝ ቀናት በኋላ ግን በኢንዶኔዚያ ሠራዊቶች ተወራ የኢንዶኔዚያ ሃያ ሰባተኛ አውራጃ ሆነች።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በብሪታንያ “ኮንሰርቫቲቭ” የቀኝ ፖለቲካዊ ቡድን መሪ የነበረችው ማርጋሬት ታቸር ከመሪነቷ ካስወገዷት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱን ስልጣን ለአገሪቷ ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ አስረከበች። ከአሥራ አምሥት ደቂቃ በኋላ ንግሥቲቱ አዲሱን የ”ኮንሰርቫቲቭ” ቡድን መሪ ጆን ሜጀርን አቅርባ፣ አዲስ አስተዳደር በጠቅላይ ሚኒስቴርነት እንዲመራ ሾመችው።