ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 16
ኅዳር ፲፮
- ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከሰተው ታላቁ ድርቅና ረሐብ እርዳታ እንዲሆን በብሪታንያ ሠላሣ ስድስት የሙዚቃ ባለሙያዎች “ባንድ ኤይድ” በሚል ስም ተሰባስበው፤ “የክርስቶስ ልደት መሆኑን ያውቁታል ወይ?” (Do They Know It's Christmas) የተባለውን ዘፈን ቀረጹ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ.ም. በአሜሪካ የ”ኢራን ኮንትራ አፌር” የተባለው የፖለቲካ ቅሌት ፈነዳ። ፕሬዚደንቱ ሮናልድ ሬጋን እና አቃቤ ሕጉ በስልጣን የነበሩ ሽርከኞች በምስጢር ለኢራን የጦር መሣሪያ እየሸጡ የሚገኘውን ትርፍ ደግሞ ለኒካራጓ ሽብርተኞች በምስጢር እንዳስተላለፉ ይፋ አደረጉ። ሁለት ባለሥልጣናት ወዲያው እንደተሻሩም ፕሬዚደንቱ ገለጹ።
- ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. የቼኮስሎቫኪያ ፌዴራላዊ ሸንጎ አገሪቱ ከሚቀጥለው የአውሮፓውያን ዘመን መግቢያ ጀምሮ ለሁለት እንድትከፈል ደነገገ። ይሄም የአሁኖቹን የቼክ ሪፑብሊክ እና ስሎቫኪያ ሉዐላዊ አገሮችን የፈጠረው ድርጊት ነው።