ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 17
መስከረም ፲፯፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት በዓለ መስቀል
- ፲፱፻፱ ዓ/ም - በትልቁ የመስቀል በዓል ቀን መኳንንቱ ከነሠራዊቱ፤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስና እጨጌ ወልደ ጊዮርጊስ ከነካህናቱ በተሰበሰቡበት በ፲ ነጥብ የተዘረዘረው የልጅ እያሱ ወንጀል ተነቦ እሳቸውን ሽረው ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥት፣ ደጃዝማች ተፈሪን ራስ ብለው አልጋ ወራሽና የመንግሥቱ እንደራሴ ተደረጉ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በፋሺስት ወረራ ጊዜ ኢትዮጵያን በመደገፍ በእንግሊዝ አገር እርዳታ በመሰብሰብ፣ የኢጣልያን ግፍ እና የምዕራባውያንን ድክመት በማጋለጥ የታገሉት ዕመት ሲልቪያ ፓንክኸርስት አረፉ። ሥርዓተ ቀብራቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተገኙበት በመንግሥታዊ ሥርዓት በኢጣሊያ ጦርነት ሰማዕት ለሆኑ ጀግኖች በተዘጋጀው መካነ መቃብር፣ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም -ሴየራ ሌዎን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።