ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሐምሌ 21
- ፲፱፻፰ ዓ/ም - ልጅ ኢያሱ ዓርብ በሌሊት ከአዲስ አበባ ተነሥተው በምድር ባቡር ድሬ ዳዋ ገቡ። በወቅቱ አላወቁትም እንጂ፣ ርዕሰ ከተማዋን ለመጨረሻ ጊዜ ያዩዋትም በዚህ ዕለት ሲሆን እዚያው ሐረርጌ ውስጥ እያሉ በመጪው መስከረም የመስቀል ዕለት ከሥልጣናቸው ተሻሩ።
- ፲፱፻፷፫ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚደንት ዶ/ር ዊሊያም ተብማን የቀብር ሥነ ሥርዓት ሞንሮቪያ ከተማ ገቡ።
- ፲፱፻፷፰ ዓ/ም - በቻይና፤ ከቤዪጂንግ ሰሜናዊ ምሥራቅ በምትገኘው ታንግሻን የተባለች ከተማ አካባቢ የተከሰተው የመሬት እንቅጥቅጥ እስከ ፯፻፶ ሺ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተገምቷል።