ውክፔዲያ
ዌኪፒዲያ የባለ ብዙ ቋንቋ የተሟላ ትክክለኛና ነጻ መዝገበ ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ነው። ማንኛውም ሰው ለውኪፒዲያ መጻፍ ይችላል። ውኪፒዲያ፣ ውኪሚዲያ የተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ከሚያካሂዳቸው ፕሮግራሞች አንዱ ነው። ወደ 272 በሚጠጉ የተለያዩ ቋንቋዎች ፅሁፎች አሉት። ውኪፒዲያ በኢንተርኔት ከሚገኙ ታዋቂ መዛግብተ ዕውቀት አንዱ ነው።
ውኪፒዲያ ድረ-ገፅን መሰረት ያደረገና ማንም ሰው በቀላሉ እንዲያስተካክለው ተደረጎ የተዘጋጀ፣ በብዙ ቋንቋዎች የሚቀርብ ነጻ የኢንተርኔት መዝገበ እውቀት ወይም ኢንሳይክሎፒድያ ነው። ውኪፒዲያ የሚለውን ስያሜ ያገኘው “ዊኪ” (ትርጉሙ ፈጣን ማለት ነው) የሚለውን ቃል ከሀዋይኛ ቋንቋ በመወሰድና “ኢንሳይክሎፒድያ” ከሚልው የእንግሊዘኛ ቃል ጋር በማዳቀል[1] ሲሆን እያንዳንዱ የውኪፒዲያ ገጽ እራሱ ከሚይዘው መረጃ በተጨማሪ አንባቢን ይበልጥ ግነዛቤ ለማስጨበጥ ከሚረዱ ሌሎች ተዣማጅ ገፆች ጋር ያለውን የትስስር መረጃም በተጨማሪነት አካቶ የያዘ ነው።
ውኪፒዲያ የተመዘገበ (የሚታወቅ) አድራሻ ሳይኖራቸው ኢንተርኔት ላይ ያለምንም ክፍያ በፈቃደኝነት የሚጽፉ የበርካታ ግለሰቦች የጋራ የትብብር ውጤት ነው። ስለሆነም ከአንዳንድ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ገደብ ከተጣለባቸው ገጾች በስተቀር ማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚና ፈቃደኛ የሆነ ሰው፤ በብዕር ስም፣ ትክለኛ ስምን በመጠቀም ወይም ደግሞ ያለምንም ስምና አድራሻ፣ ውኪፒዲያ ላይ የፈለገውን ሀሳብ የማስፈርና አስተዋጾ የማድረግ አሊያም ቀድሞ በሰፈረ ጽሁፍ ላይ ተጨማሪ መረጃን የማካታት፣ ስህተትን የማረምና የማስተካከል ፈቃድ ተሰጥቶታል።[2]
ውኪፒዲያ ከተመሰረተበት ከ2001 እ.ኤ.አ. ጀምሮ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለና በብዛት ከሚጎበኙና ኢንተርኔት ላይ ከሚገኙ በረካታ የማጣቀሻ ድረ-ገጾች መካከል አንዱ ሲሆን 2011 እ.ኤ.አ. መጋቢት ወር ብቻ ከ400 ሚሊዎን በላይ አዳዲስ ጎብኝዎች ድረገጹን እንደጎበኙት ኮም ስኮር ያካሄደው የጥናተ ዘገባ ያመለክታል። ውኪፒዲያ ከ82,000 በላይ አርታኢዎች፣ ከ270 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያጠናቀሯቸውን ከ19,000,000 በላይ የሚሆኑ መጣጥፎችን አካቶ የያዘ ድረ-ገጽ ነው። ውኪፒዲያ በአሁኑ ጊዜ 3,874,529 የእንግሊዘኛ መጣጥፎችን የያዘ ሲሆን በየቀኑ ከመቶ ሺህ በላይ ጎብኝዎች እንደሚጎበኙትም ይገመታል። በተጨማሪም በተለያዬ የአለም ክፍል የሚኖሩ ግለሰቦች በሚያደርጉት የጋራ አስተዋጽኦ በየቀኑ ከአስር ሺህ በላይ መጣጥፎች የተለያዩ ማስተካከያዎች የሚደረግባቸው ሲሆን ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ መጣጥፎች ደግሞ ውኪፒዲያን በየቀኑ ይቀላቀላሉ።[3]
ምንም እንኳን መሰረታዊ የውኪፒዲያ መርሆች የሚባሉት አምስት ቢሆኑም ይህንኑ መዝገበ-ዕውቀት (ኢንሳይክሎፒዲያ) ይበልጥ ለማሻሻልና ለማጎልበት የሚያግዙ ሌሎች በርካታ ፖሊሲዎችና መመሪያዎች በውኪፒዲያ ማህበረሰብ ተቀርጸው ተግባር ላይ የዋሉ ሲሆን ነገር ግን እነዚህን መሰረታዊ መመሪያዎችና ደንቦች አስተዋጾ ማድረግ ካልጀመረ በስተቀር ማንኛውም ሰው የማወቅ ግደታ የለበትም።[4]
በሌላ በኩል፣ ውኪፒዲያ አንድ ሰው ካለው የሙያ ችሎታ ይልቅ ለሚያበረክተው አስተዋፆ ትልቅ ግምት የሚሰጥ በመሆኑ፣ በተለያየ የእድሜ ክልል፣ ባህልና መነሻ (ዳራ) የሚገኝ ማንኛውም ሰው የውኪፒዲያ አስገዳጅ ፖሊሲዎችን አሟልቶ እስከተገኘ ድረስ፣ ውኪፒዲያ ላይ የፈለገውን መጣጥፍ እንዳንድስ የመጨመር አሊያም ማንኛውም ውኪፒዲያ ላይ የሚገኝ ሌላ ጽሑፍ፣ ማጣቀሻና ምስል የማየት የማሻሻልና የማረም አንዳደም ሙሉ ለሙሉ የመለዎጥና ፈቃድ አለው። በመሆኑም ውኪፒዲያ በተለያዩ አስተዋጾ አድራጎዎች በየጊዜው ማሻሻያ የሚደረግበት እንደመሆኑ መጠን፣ አዲስ ከሚካተቱት መጣጥፎች ይልቅ ቀደም ሲል በድረ ገጹ የተካተቱ መጣጥፎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታረሙና እየተሻሻሉ የሚሄዱ በመሆናቸው የተሻለ የሐሳብ ጥራት፣ የመረጃ ሚዛናዊነትና ምሉእነት እንደሚኖራቸው ይታመናል።
የውክፔዲያ አመሰራረት
ለማስተካከልዊክፔዲያ ነፃ ኦንላይን መዝገበ-ዕውቀትን (free encyclopedia) ለመፍጠር አላማ አድርጎ የተመሰረተና ቀደም ሲል ኑፔዲያ (Nupedia) በመባል የሚታወቅ ፕሮጀክት ውጤት ነው። ኑፔዲያ ምንም እንኳን የተሻሻለ የዕርስ-በርዕስ መገማገሚያ (peer review) መንገዶችን አካቶ የያዘና ሙያዊ ብቃት ያላቸው መጣጥፍ አቅራቢዎችን የሚጠይቅ ፕሮጀክት የነበረ ቢሆንም መጣጥፎችን አትሞ ለማውጣት ረጅም ጊዜን ይጠይቅ ነበር። በመሆኑም ይንንም ችግር ለመቅረፍ፣ በ2000 እ.ኤ.አ. የኑፔዲያ መስራቹ ጂሚ ዌልስና በዚሁ ፕሮጀክት ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ላሪ ሳንገር[5][6] የተባለ ሌላ ግለሰብ ኑፔዲያን እንደት ማሻሻልና ሌሎች ተጨማሪ ገፅታዎችን አካቶ የሚይዝ ፕሮጀከት ማደረግ እንሚቻል የጋራ ውይይት አደረጉ።[7] በውይይታቸውም ወቅት እንደ ግብአት የተጠቀሟቸው አብዛሐኛዎቹ ምንጮች አንድ የዊኪ ድረ-ገጽ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸውን አስተዋፆ ማበረከት የሚችሉበት መዳረሻ ተደርጎ ድዛይን ሊደረግ እንደሚችል አመላከቱዋቸው። በዚህም መሰረት ማንኛውም ሰው የራሱን አድስ አስተዋፆ ማበርከትና ብሎም ሌሎች የቀረቡ መረጃዎችን ማስተካክልና ማረም እንዲያስችል ተደርጎ ዲዛይን የተተደረገው የመጀመሪያው የኑፔዲያ የዊኪ ገፅ እ.ኤ.አ ጥር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. አየር ላይ ዋለ።[8]
ነገር ግን ሌሎች የኑፔዲያ ፕሮጀክት አካል የነበሩ አርታኢዎችና ሀያሲዎች በኑፔዲያ ፕሮጀክት ላይ የተደረገውን የማሻሻያ ለውጥ በተለየም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የየራሳቸውን አስተዋሶ ማበርከት የሚያስችልን ድረ ገፅ(ዊኪ) ቅርፅ እዲይዝ ተደርጎ መሻሻሉን በመቃዎማቸው፣ የተሻሻለው የኑፔዲያ ፕሮጀክት አድስ የስያሜ ለውጥ በማድረግና “ዊክፔዲያ” በመባል በራሱ አድራሻ (www.wikipedia.com) አንዳንዶች ዛሬ “የዊክፔዲያ ቀን” እያሉ በሚጠሩት ጥር 15 ቀን በይፋ ስራውን ጀመረ።[9]
ለውክፔዲያ ሳንዲዬጎ የሚገኘውንና የመጀመሪያው የድረ-ገፁ መቀመጫ በመሆን ያገለገለውን ሰርቨር ኮምፒውተርና የመረጃ ማስተላለፊያ መስመሩን (bandwidth) በርዳታ የለገሰው ጂሚ ዌልስ ነበር። በተጨማሪም በራሱ በጂሚ ዌልስ እና በሌሎች ሁለት ጓደኞቹ የተቋቋመውና በአነስተኛ የኢንተርኔት የማስታዎቂያ ስራዎች ላይ የተሰማራ ቦሚስ (bomis) የሚባል ድርጅት ሰራተኞች የነበሩና ባሁኑ ጊዜም እየሰሩ የሚገኙ ሌሎች ግለሰቦችም የራሳቸውን አስተዋፆ ለዊክፔዲያ አበርክተዋል። በዚህ ረገድ ከሚጠቀሱት፣ የቦሚስ ተባባሪ መስራችና በአሁኑ ጊዜ የድርጂቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን እያገለገለ የሚገኘው ቲም ሸልና ፕሮገራመሩ ጃሰን ሪቺ ይጠቀሳሉ። በሌላ በኩል ዊክፔዲያ አሁን ወደ ሚታወቅበት www.wikipedia.org የአድራሻ ለውጥ ያደረገው ለትርፍ የማይንቀሳቀሰውና የራሱ የዊክፔዲያ እህት ኩባኒያ የሆነው “ዊክፔዲያ ፋውንደሽን” ከተቋቋመ በሗላ ነበር።[10]
ውክፔዲያ ምንም እንኳ መጀመሪያ የተመሰረተው እንግሊዘኛ ቋንቋን መሰረት አድርጎ ቢሆንም እ.ኤ.አ ከግንቦት 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ሌሎች አዳድስ ቋንቋዎችን በማካተት የበርካታ ቋንቋዎች መዳረሻ ለመሆን ችሏል። ከነዚህም መካከል ካታልኛ፣ ቻይንኛ፣ ጀርመንኛ፣ ሞስኮብኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ዕብራይስጥ፣ ጣሊያንኛ፣ ጃፓንኛ፣ ፖርቹጋልኛና ስፓንሽኛ በግንባር ቀደምትነት ዊክፔድያን የተቀላቀሉ ቋንቋዎች ሲሆኑ፣ አረብኛ፣ ሀንጋሪኛ፣ ፖሎንኛና ሆላንድኛ ከላይ የተጠቀሱትን ቋንቋዎች በቅርብ እርቀት ተከትለው የተቀላቀሉ ሌሎች ቋንቋዎች ናቸው። በሌላ በኩል በጥር 2012 እ.ኤ.አ. በተደረገ ጥናት ዊክፔድያ ከ31 ሚሊዎን በላይ በሚሆኑ የተመዘገቡ የዊኪፒዲያ አስተዋፆ አድራጎዎችና በመላው አለም በሚገኙ ሌሎች ስፍር ቁጥር የሌላቸው ያልተመዘገቡ (የማይታወቁ) አስተዋፆ አድራጎዎች በ283 ቋንቋዎች ከ20 ሚሊዎን በላይ የሚሆኑና ማንምሰው በነፃ ሊገልባቸው የሚችሉ መጣጥፎችን አካቶ መያዙ ተረጋግጧል። በተጨማሪም ከጠቅላላው የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ውስጥ 14.5% ዊክፔዲያን እንደሚጎበኙ ተረጋግጧል።[11]
የንግድ ምልክትና የኮፒራይት ህግ
ለማስተካከልውክፔድያ ንብረትነቱ ዊክሜዲያ ፋውንደሽን የሚባል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የተመዘገበ ህጋዊ የንግድ ምልክት ነው።
የውክፔዲያ አስተዋፆ አድራጊዎች
ለማስተካከልማንኛውም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚና ፈቃደኛ የሆነ ሰው ከአንዳንድ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ገደብ ከተጣለባቸው ገጾች በስተቀር ውክፔዲያ ላይ ስለተለያዩ ጉዳዮች (በህዎት ያሉ ሰዎችን ስም የሚያጠፉና ሌሎች የተከለከሉ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ሳይጨምር) የፈለገውን ጽሁፍ የማስፈር አሊያም ስህተት የሆነን ጽሑፍ የማረምና የማስተካከል ፈቃድ ተሰጥቶታል። ይህም ያልተገደበ ፈቃድ ዊክፔዲያ በርካታ መጣጥፎችን እንዲኖሩት ያስቻለው ሲሆን፣ ከቀላል የድረ-ገጹ ተጠቃሚዎች (አንባቢዎች) ጨምሮ እስከ 91000 የሚደርሱ የተለያዩ የሙያ ባለቤት የሆኑ ግለሰቦችና በቋሚነት ዊክፔዲያን አርትኦት የሚያደርጉ ፈቃደኛ አስተዋፆ አድራጊዎችን አሉት። በመሆኑም ምንም እንኳን የድረገፁ ባለቤት ዊክፔዲያ ፋውንደሽን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ በድረ-ገፁ ላይ በሚዎጡ የፅሁውፍ ስራዎችና የድረ-ገፁን የቀን ተቀን እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠሩ ረገድ የላቀ ተሳትፎ አይታይበትም።
በተጨማሪም ይህንንም የበለጠ ለማጎልበት ይረዳ ዘንድ፣ የተለያዩ የዊክፔዲያ ተጠቃሚዎችና አባሎች ግለሰባዊ ማንነታቸው/ሙያቸው/ እንደተጠበቀ ሆኖ የተሻሻለና ጥራት ያላቸው ስራ ማበርከት ይችሉ ዘንድ የተለያዩ መፍትሔዎች ተነድፈው ተግባራዊ ሆነዋል። ከነዚህም መካከል አርታኢዎች የተላያዩ ገፆችን ማስተካከልና መፍጠር የሚችሉ ሲሆን ፕሮገራመሮች ደግሞ የአርትኦት ችግር ያለባቸውን ገፆች በቀላሉ ለመከታተል የሚያስችሉ ፐፕሮገራሞችን በየጊዜው ያዘጋጃሉ። በተጨማሪም በመረጃዎች አቀራረብ ዙሪያ አንዳንድ አለመግባባቶች በአርታኢዎች መካከል ሲፈጠሩ፣ አርታኢዎች በጋራ በመሰባስብና በመወያየት ተጨባጭና የተሻለ የነገሩን/ሀሳቡን እውነታ ይወክላል የሚሉትን በመርጥ እንዲያፀድቁ የሚደረግበት አሰራርም አለ።
የአስተዋፆ ማስታወሻዎች
ለማስተካከልበተለያዩ የዊክፔዲያ ገፆች ላይ የሚገኙ ጽሑፎች የበርካታ አስተዋፆ አድራጊ ሰዎች የጋራ የትብብር ውጤቶች ናቸው። በመሆኑም ማንኛውም ለውክፔዲያ ገፅ አስተዋፆ ያደረገ ግለሰብ ፣ ገፁን በመፍጠር ሂደት ውስጥ አስተዋፆ ያበረከቱ ግለሰቦች በሚመዘገቡበት የገፁ ታሪክ መዝገብ ውስጥ የሚካተትና ያደረገው አስተዋፆም የሚመዘገብ ሲሆን ይህም ለማንኛውም ሰው በግልፅ እንዲታይ ተደርጎ ከገፁ ጋር ተያያዥ ሆኖ የሚቀርብ ነው። ምስሎችንና ሌሎች ሜዲያዎችን በተመለከተ የተመዘገበን የአስተዋፆ አድራጊነት፣ የባለቤትነት ድርሻን ወይም ደግሞ ሌሎች የመረጃ ምንጮችን በተመለከተ መረጃን ለማዎቅ ካስፈለገ፣ የተፈለገው ምስል ላይ በኮምፒውተራችን ማውስ ጠቅ በማድረግ ወይም ደግሞ በአቅራቢያው የሚገኝን የመረጃ መስጫ ምልክት (icon) በመጫን መመልከት (ማግኘት) ይቻላል።
ውክፔዲያን በተሻለ መጠቀም
ለማስተካከልውክፔዲያን በመጠቀም መረጃን በተሻለ ማግኘት
ለማስተካከልውክፔዲያን በቀን ከሚጎበኙ የድረ-ገጹ ተጠቃሚዎች መካከል ብዙዎቹ በድረ-ገጹ ላይ ሌሎች እንዲጎበኙ ያስቀመጡዋቸውን (ያጋሩዋቸውን) መረጃዎች ለማገኘት ሲሆን ሌሎች በርካቶች ደግሞ ያላቸውን መረጃ/እውቀት በዚሁ ድረ-ገጽ በመታገዝ ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለማጋራት ነው። በዚሁ ተመሳሳይ ቅፅበት ደግሞ ሌሎች በርካታ መጣጥፎች ማሻሻያ ሲደረግባቸው፣ ሌሎች ስለ በርካታ ጉዳዮች የሚዳስሱ መጣጥፎች ደግሞ እንደ አድስ እየተጻፉ ውክፔዲያን ይቀላቀላሉ። በመሆኑም እስካሁን ውክፔዲያን ከተቀላለቀሉ መጣጥፎችም መካከል ከ3000 በላይ የሚሆኑ መጣጥፎች በዊክፔዲያ ማህበረሰብ “የምንጊዜም ምርጥ መጣጥፎች” በሚል የተመረጡ ሲሆን ከ13000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ «የተሻሉ መጣጥፎች» በሚል የተመረጡ ናቸው። በተጨማሪም ውክፔዲያ ላይ የሚገኙ መረጃዎች በተለያዩ የመረጃ የደረጃ ክፍልፍሎሽ (ዝርዝሮች) ስር እየተጠናቀሩ የሚቀርቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተሻለ የመረጃ የክፍፍሎሽ ይዘት ያላቸው መጣጥፎች “የምንጊዜም ምርጥ ዝርዝር” በሚል ጠመርጠዋል። በሌላ በኩል ውክፔዲያ የተለያዩ አርዕስቶች/ጉዳዮችን በተመሳሳይ ቦታ ለማጋራት የሚያስችል አስራርን የሚከተል በመሆኑ ተመሳሳይ ሃሳቦችን በተመሳሳይ አርዕስቶች ዙሪያ በማደራጀትና የተለያየ ይዘት ያላቸውን መረጃዎችን በተመሳሳይ መዳረሻ በማቅረብ ረገድ ውክፔዲያ “የምንግዜም ምርጥ መዳረሻ” በሚል የተመረጠ ድረ-ገጽ ነው።[12]
በተለያዩ መጣጠፎች ላይ የተደረጉ የመረጃ ማሻሻያዎችን በሁለት መንገድ መከታተል ይቻላል። በተለያዩ ገፆች በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ለመመልከት በዋናው ገፅ የሚገኘውና «በቅርብ ጊዜ የተለወጡ» የሚል ርዕስ ያለውን ጽሁፍ በመጫን መመልከት ይቻላል። ማንኛውንም ለውጥ ለመመልከት ከተፈለገ ደግሞ በዋናው ገፅ የሚገኘውን “ማንኛውንም ለማየት” የሚል ርዕስ ያለውን ጽሁፍ በመመጫን መመልከት ይቻላል።
በሌላ በኩል ውክፔዲያ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ በተጨማሪ አማርኛን ጨምሮ በሌሎች ቋንቋዎችም አገልግሎት ከመስጠቱ ባሻገር፣ የተሻሻለና ቀላል የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ ሌሎች ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ፕሮጀክቶች ማለትም፤ መዝገበ-ቃላት፣ ጥቅሶች፣ መጸሐፍት፣ መመሪያዎች፣ ሳይንሳዊ የመረጃ ምንጮችና የዜና አገልገሎትና ሌሎች መሰል አገልገሎቶችን ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ያቀርባል። እነዚህም የተለያዩ አግልግሎቶች፣ ከውክፔዲያ ማህበረሰብ በተጨማሪ በተናጥል በሚገኙ ሌሎች ማህበረሰቦች ክትትል፣ ቁጥጥርና ማሻሻያዎች የሚደረጉባቸው ሲሆኑ አብዛሀኛዎቹ መጣጥፎችም በሌሎች የመረጃ መጋሪያ ድረ-ገጾች በቀላሉ የማይገኙ ናቸው።
ውክፔድያ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች
ለማስተካከልየሚከተሉት ዋና የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የውክፔድያ ድረ-ገጽና መርሀገብር ለተናጋሪዎቻቸው አላቸው።
- አማርኛ ውክፔድያ - አሁኑ የሚያነቡት
- ኦሮምኛ ውክፔድያ - om:
- ትግርኛ ውክፔድያ - ti:
- ሶማልኛ ውክፔድያ - so:
- አፋርኛ ውክፔድያ - aa: (ተዘግቷል ።)
የአፋርኛ ውክፔድያ የተዘጋበት ምክንያት የአፋርኛ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች ጉድለት በኢንተርኔት ላይ ስላለ ነው። (ደግሞ ኢንተርኔት በኢትዮጵያ ይዩ።) ዳሩ ግን ጊዜያዊ የአፋርኛ ማዘጋጀት ቦታ በincubator:Wp/aa/Main Page ተደርጓል። ሌሎች የዓለም ልሳናት «ጊዜያዊ» ውክፔድያዎች ወዘተ. በዚህ ይዘረዘራሉ፦ incubator:Incubator:Wikis። መዝገበ ዕውቀት ለመጽሐፍ የሚችሉ ለቋንቋውም ቅልጥፍና ያላቸው አዛጋጆች በኖሩበት ጊዜ፣ እነዚህ «ጊዜያዊ» መርሃግብሮች ደግሞ የገዛ ድረ-ገጾቻቸውን ሊያገኙ ይችላሉ። ከዚህ በቀር በማንኛውም ሌላ ቋንቋ «ጊዜያዊ» ውክፔድያ በጥያቄ መጀምር ቀላል ነው።
መሰረታዊ የውክፔዲያ የገፅ ለገፅ ዝውውር
ለማስተካከልሁሉም በውኪፔዲያ የሚገኙ መጣጥፎች እርዕስ በርሳቸው እንዲገናኙ ተደርገዋል። ማንኛውም የተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ያለው ጽሁፍ ስለተሰመረው አርዕስት የተሻለና የተብራራ መረጃ ሊሰጥ ከሚችል ሌላ ገፅ ጋር እንደተሳሰረ የሚያመለክት ሲሆን የኮምፒውተራችን ማውስ በዚህ በተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ባለው ማንኛውም ጽሁፍ ላይ በመጠቆም የተቀመጠው ትስስር ከየትኛው ገፅ ጋር እንደሆነ መመልከት ይቻላል።
አንባቢው እንደዚህ አይነት ትስስር ያላቸውን ሀሳቦች ለበለጠ ለመረዳት ከፈለግ በማንኛውም በተሰመረና ሰማያዊ ቀለም ባላው አርዕስት ላይ ክሊክ በማድረግ ተጨማሪ ማብራሪያ ማግኝት ይችላል። ከዚህ አይነት የገጽ-ለገጽ ትስስሮሽ በተጨማሪ አንባቢን ከሌሎች ከተለያዩ ጉዳዮች ጋር እንዲያገናኙ ሆነው የተፈጠሩ ሌሎች ትስስሮች ይኖራሉ። ለምሳሌ ያክል ከቀረበው መጣጥፍ ላይ ወደሚገኘው የመጨረሻ ገጽ የሚዎስዱ፣ ከሌሎች ውጭያዊ ጠቃሚ ድረገፆች ጋር የሚያገናኙ፣ ወደ ማጣቀሻ ምንጮች የሚወስዱና በተለያዩ ደረጃዎች/አርዕስቶች በተዋቀረ ገፅ ላይ በቀላሉ ከአንድ አርዕስት ወደ ሌላ አርዕስት ለመንቀሳቀስ የሚያገዙ ትስስሮች ይገኙበታል።ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ መጣጥፎች እንደ መዝገበቃላት መፍቻዎች፣ የድምፅ የመፀሐፍ ንባብ፣ ጥቅሶችን፣ የቀረበው መጣጥፍ በሌላ ቋንቋ ወደ ተጻፈ የመጣጥፉ ግልባጭ (ኮፒ) የሚወስዱና ከሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ከያዙ እህት ፕሮጀክቶች ጋር የሚያሰተሳስሩ ይገኙበታል።
ውኪፔዲያን ለምርምር መሳሪያነት መጠቀም
ለማስተካከልእንደ ዊኪ (ፈጣን) የመረጃ ፍይልነታቻው በውኪፔዲያ ውስጥ የሚገኙ መጣጥፎች በሁሉም ረገድ የተሟሉ ናቸው ብሎ ለመገመት ያዳግታል። ከዚህ ይልቅ የዊኪፔዲያ የተለያዩ መጣጥፎች፣ በተከታታይ አርትኦትና ማሻሻያዎች እየተደረገባቸው ስለሚሄዱ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ የተሻሻለንና ትክክለኛ የሆነ መረጃን እየያዙ እንደሚመጡ ይታመናል። ስለሆነም ማንኛው የውኪፔዲያ ተጠቃሚ፤ ሁሉም መጣጥፎች ከመነሻቸው አንድ ኢንሳክሎፔዲያ ሊያሟላው የሚገባውን የጥራት ደረጃ ሊያሟሉ እንደማይችሉና ምናልባትም የተሳሳተ ይዘት ያላቸው ወይም አከራካሪ የሆኑ መረጃዎችን ሊይዙ እንደሚችሉ መገንዘብ ይኖርበታል። በርገጥም ብዙ መጣጥፎች ከመነሻቸው አጭርና የአንድዮሽ ምልከታን ብቻ በመያዝ የሚጀመሩ ሲሆን ቀስ በቀስ ግን የተለያዩ ምልከታዎችንና መረጃዎችን በማካተት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል ደረጃ ሙሉና ሁለገብ እየሆኑ የሚሄዱ ናቸው። [13]
ለዚህም እንደምከንያትነት የሚጠቀሰው፣ በርካታ የመጣጥፍ አርታኢዎችና አዘጋጆች፣ የሚያቀርቡትን መጣጥፍ ሁለገብ ይዘት እንዲኖረው ከማድረግ ይልቅ ብዙውን ጊዜ የሚያጠነጥኑት በራሳቸው የግል ፍላጎትና የአንድዮሽ ምልከታ ላይ ብቻ በመሆኑ እንደዚህ አይነት የይዘት ችግር ያለባቸውን መጣጥፎች እንደገና ላማሻሻልና ሚዛናዊ መረጃን እንዲይዙ ለማድረግ ረዘም ያለ ጊዜ የሚጠይቁ ሲሆን ምናልባትም እስከ አንድ ወር ጊዜ ድረስ የሚያስፈልጋቸው ይኖራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የዚህ አይነት ችግር ያላባቸውን መጣጥፎች ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት የተለያዩ አርታኢዎች የየራሳቸውን ድርሻ ስለሚያበረክቱ መጣጥፎቹን ሁለገብ እና ሚዛናዊ ለማድረግ የሚድረገውን ጥረት በቀላሉ ለማሳካት ክፍተኛ አስተዋፆ አላቸው። በተለይም ደግሞ በተለያዩ የመጣጥፍ አርታኢዎች መካከል የሚፈጠርን አልመገባባት በቀለላሉ ለመምፈታት የሚያሰችሉ የውክፔዲያ የራሱ የሆኑ ብዛት ያላቸው ውስጣዊ የድርጅት አሰራሮች ያሉት በመሆኑ በዝህ ረገድ ያሉ አላስፈላጊ ችግሮችን በቀላሉ ማስወገድ ይቻላል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቢያንስ በመርህ ደረጃ አንድ የዊክፔዲያ መጣጥፍ ሊያሟላ ከሚገባቸው መሰረታሢ ነጥቦች መካከል፣ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል። በጥራት የተጻፈ፣ ሚዛናዊ የሆነ መረጃን የያዘ መሆን፣ ከዎገናዊነት የፀዳና መዝገባዊ ይዘት ያለው ሲሆን በተጨማሪም፣ የተሟላ፣ ሊጠቀስና ሊረጋገጥ የሚችል መረጃን የያዘ የሚሉት ይገኙበታል። በዚህም ረገድ ይህንን ስታንዳርድ ያሟሉና ከጊዜ ወደ ጊዜ በሟሟላት ላይ የሚገኙ በርካታ መጣጥፎች ያሉ ሲሆን እነዚህንም የተለያዩ የመጣጥፍ ደረጃ መለኪያ ስታንዳርዶችን አሟልተው የተገኙ በረካታ መጣጥፎች “የምንግዜም ምርጥ መጣጥፎች” በሚል ስያሜ ይታወቃሉ። ይህንንም ለማመልከት መጣጥፉ በሚገኝበት ገጽ የላይኛው የቀኝ ጥግ ላይ ትንሽ የኮኮብ ምልክት እንዲቀመጥ ይደረጋል። ነግርግን ሌሎች በረካታ መጣጥፎች፣ የተሟላ የመረጃ ማጣቀሻ ያላስቀመጡ፣ በበቂ ሁኔታ ያልተብራሩ አሊያም በፊት ከነበራቸው የተሻለ ይዘት በተጨማሪ ሌሎች ገና ያልተብራሩ አዳድስ ክፍሎችን ያካተቱ ስለሚሆኑ ይህንን “የምንግዜም ምርጥ መጣጥፎች “ የሚል ደረጃ ለማግኘት ከአንድ ወር እስከ አንድ አመት ጊዜን የሚጠይቅ የማሻሻል ስራና ያላሰለሰ ጥረትን የሚጠይቁ ናቸው።
ስለሆነም ምንም እንኳን ውክፔዲያ በብዙ ረገድ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም የተለያዩ መጣጥፎች የተለያየ የሀሳብ ጥልቀትና ጥራት ሊኖራቸው ስለሚችል ዊክፔዲያን እንደ አንድ የምርምር ማጣቀሻነት ከመጠቀም ጎን ለጎን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ይመከራል። በዚህ ረገድ መረጃ በመስጠት ተጠቃሚን የሚያግዙ ገፆች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ከነዚህም መካክል የማመላከቻና የመረጃ ገጽንና ስለ ውክፔዲያ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭነት የተደረጉ የሶስተኛ ወገን ጥናቶችን መመልከት ይቻላል።
ውክፔዲያ ከሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነፃጸር
ለማስተካከልውክፔዲያ ቀደም ሲል በስፋት ይውሉ ከነበሩ የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች[14] ጋር ሲነፃጸር ከፈተኛና የራሱ የሆነ ጠቀሜታ አለው። በመጀመሪያ ደረጃም አነስተኛ የህትመትና የማስፋፋት ወጭና የሚጠይቅ መሆኑና ዝቀተኛ የሆነ የጎንዮሽ አካባቢያዊ ተፅኖች ያሉት መሀኑን ማንሳት ይቻላል። በሌላ በኩል ምንም አይነት የህትመት ስራ የማይፈለግ በመሆኑ ኮምፒውተሮች የራሳቸው የሆነ አካባቢያዊ ተጽኖ ይኖራቸዋል።
በተጨማሪም ሁሉንም አይነት መግለጫዎችን በአንድ ገጽ አካቶ ከመያዝ ይልቅ እርስበርስ የሚዛመዱና በሌሎች የተለያዩ ገጾች የተብራሩ ጉዳዮችን ከአጫጭር ማጠቃለያዎች ጋር አጣምሮ በማቀረብ በቀላሉ መረጃን ለማግኘት ይረዳል። በመጨረሻም እንዴ ሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች የተወሰነ የአርትኦትና የማሻሻያ ጊዜን የማይጠይቅ በመሆኑ፣ ውክፔዲያ ከሌሎች የህትመት ኢንሳይክሎፕዲያዎች ጋር ሲነጻጸር አጭር የአርትኦት ጊዜን የሚጠይቅና በማንኛውም ጊዜና ሰአት መሻሻሎችን በማደረግ መጣጠፎች ወቅታዊና ጊዜውን የተበቀ መረጃን ይዘው እንዲቀጥሉ የሚያስችል ዘመናዊ አሰራርን ይፈቅዳል እና መረጃ ለማንበብ አደገኛ ጣቢያ።
ማጣቀሻዎች
ለማስተካከል- ^ “wiki” in the Hawaiian Dictionary, Revised and Enlarged Edition, University of Hawaii Press, 1986
- ^ ^ "Wikipedia's Jimmy Wales Speaks Out On China And Internet Freedom". Huffington Post. Retrieved September 24, 2011. "Currently Wikipedia, Facebook and Twitter remain blocked in China"
- ^ Larry Sanger, Why Wikipedia Must Jettison Its Anti-Elitism, Kuro5hin, December 31, 2004.
- ^ ^ "Wikipedia.org Site Info". Alexa Internet. Retrieved November 9, 2011.
- ^ Mike Miliard (March 1, 2008). "Wikipediots: Who Are These Devoted, Even Obsessive Contributors to Wikipedia?". Salt Lake City Weekly. Retrieved December 18, 2008.
- ^ Kaplan Andreas, Haenlein Michael (2014) Collaborative projects (social media application): About Wikipedia, the free encyclopedia. Business Horizons, Volume 57 Issue 5, pp.617-626
- ^ How I started Wikipedia, presentation by Larry Sanger
- ^ ^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.
- ^ ^ a b Richard M. Stallman (June 20, 2007). "The Free Encyclopedia Project". Free Software Foundation. Retrieved January 4, 2008.
- ^ Jonathan Sidener (December 6, 2004). "Everyone's Encyclopedia". The San Diego Union-Tribune. Retrieved October 15, 2006.
- ^ Size of Wikipedia
- ^ http://stats.wikimedia.org/wikimedia/squids/SquidReportPageViewsPerCountryOverview.htm Wikimedia
- ^ ^ "Wikipedia:Verifiability". Retrieved February 13, 2008. "Material challenged or likely to be challenged, and all quotations, must be attributed to a reliable, published source."
- ^ ^ "Encyclopaedia Britannica and Nature: a response". Retrieved July 13, 2010.
የውጭ መያያዣ
ለማስተካከል- ውክፔዲያ ኹኔታ ከ10 አመት በኋላ - አጭር ቪዲዮ በዩ ቱብ ላይ (እንግሊዝኛ)