ኣጣርድ ወይም ሜርኩሪ፡ (ምልክት፦☿) መሬት በምትገኝበት ማለትም ሚልክ ዌይ ተብሎ በሚጠራው ረጨት ወይም የከዋክብት ስብስብ ውስጥ የሚገኝ ፈለክ ነው። ይህ ፈለክ ከፀሐይ ባለው ርቀት ቅርቡ (1ኛው) ነው። ከበስተኋላው ዘጠኙም ፈለኮች ማለትም ቬነስመሬትማርስጁፒተርሳተርን ኡራኑስነፕቲዩን እና ፕሉቶ ይገኛሉ።ሜርኩሪ ጠንካራ ፣ የብረት ሰልፋይድ የውጪውን ንጣፍ ፣ ጥልቀት ያለው ፈሳሽ ንጣፍ እና ጠንካራ የውስጥ ኮርትን የሚሸፍን ጠንካራ የሰልፈር ክሬን እና ምንጣፍ ያለው ይመስላል።

Mercury in color - Prockter07 centered.jpeg

ስሙ «ኣጣርድ» የተወረደ ከአረብኛው «ኡጣሪድ» ነበር። በድሮ ጊዜ ይህ የአረመኔ ጣዖት ስም ነበር። አሕዛብ ይህ የጥበብ ጣኦት እንደ ነበር ስላመኑ፣ የፈለኩ ስም ከዚህ ጣኦት ስም መጥቶ በየቋንቋው ይለያይ ነበር። ስለዚህ የፈለክም ሆነ የጣኦት ስም በፋርስኛ «ቲር»፣ በባቢሎንኛ «ናቡ»፣ በጥንታዊ እንግሊዝኛ «ዎደን»፣ በግሪክ «ሄርሜስ»፣ በሮማይስጥም «ሜርኩሪዩስ» ሆነ። «ሜርኩሪ» የሚለው እንግሊዝኛ ሲሆን ከዚሁ ሮማይስጥ ስም መጣ። በዕብራይስጥ ግን ስሙ «ኮካብ ሐማህ» ወይም «የፀሐይ ኮከብ» ይባላል። በአፋን ኦሮሞ ደግሞ «ቃሙ ዳለቸ» ሲባል ፍቺውም « ግራጫ በረሃ» ነው። በሶማለኛ ደግሞ «ዱሳ» ይባላል።

ይዘትEdit

ይህ ፈለክ በዚህ ረጨት ውስጥ ከሚገኙ ፈለኮች በመጠኑ ትንሹ ነው። ዲያሜትሩ 2439.7 ኪ.ሜ ብቻ ነው። መዋቅሩ ከመሬት ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ቋጥኞች የበዙበት ነው።