ጥንታዊ እንግሊዝኛ (Englisc /ኧንግሊሽ/) በእንግሊዝ አገር ከ440 ዓ.ም. ገደማ እስከ 1100 ዓ.ም. ያሕል የተናገረ ቋንቋ ነበር። ዛሬ ጀርመንዴንማርክ ከተባሉት አገሮች ፈልሰው በእንግሊዝ በተስፈሩት ሕዝብ የተናገሩበት ሲሆን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ቀድሞ አይነት ነው። ሆኖም በቃላትም ሆነ በስዋሰው ከዘመናዊ እንግሊዝኛ በጣም ይለያል። ቅርብ ዘመዶቹ ጥንታዊ ፍሪዝኛ እና ጥንታዊ ሴክስኛ ናቸው።

«ጎደስ ፌውሕ ኦንድ ቺሪቼየን ትወልቨ ዪውልደ።» («የአምላክ ነዋይና የቤተክርስቲያን፣ ፲፪ እጥፍ») በማለት ከሁሉ ጥንታዊ የታወቀው የእንግሊዝኛ ዓረፍተ ነገር፣ የአሰልበርህት ህግጋት (594 ዓም)፣ ይጀምራል። ይህ በ1100 ዓም ግድም የተሠራ ቅጂ ነው።

ጥንታዊ እንግሊዝኛ በርካታ ተመሳሳይ ቀበሌኞች ነበሩት። በተለይ በስሜን እንግሊዝ የኖሩት የአንገሎች መነጋገርያ በደቡብ ከኖሩት ከሴክሶች ትንሽ ተለያየ።

ከ800 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ ስሜኑ በቫይኪንጎች ስለተወረረ በንጉስ አልፍሬድ ጊዜ የሴክሶች ቀበሌኛ ይፋዊ ሁኔታ አገኘ። ቢሆንም የቫይኪንጎች ቋንቋ ኖርስኛ ከጥንታዊ እንግሊዝኛ ጋር ዝምድና ነበረውና ከኖርስኛ አያሌው ቃላት ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ለምሳሌ የእንግሊዝኛ ቃላት sky /ስካይ/ (ሰማይ) leg /ለግ/ (እግር) እና they /ዘይ/ (እነሱ) የደረሱ ከኖርስኛ ነበር። በእንግሊዝ ኗሪዎች ቋንቋ (በጥንታዊ እንግሊዝኛ) እነዚህ ቃላት 'ሄዮቮን'፣ 'ሽያንካ' እና 'ሂዬ' ሆነው ነበር።

የተማሩ ሰዎች (መምህራን ወይም ቄሶች) በብዛት የሮማይስጥ ዕውቀት ስለነበራቸው ደግሞ ከሮማይስጥ ተጽእኖ አንዳንድ ቃላት የዛኔ ወደ እንግሊዝኛ ገቡ። ንጉሥ አልፍሬድ እራሳቸው ብዙ መጻሕፍት ከሮማይስጥ አስተረጎሙ።

ኖርማኖች እንግሊዝን በ1059 ከወረሩ ጀምሮ እንግሊዝኛ ከትምህርት ቤት ስለ ተከለከለ በየጥቂቱ ባሕርዩ እጅግ ተለወጠ።

በጥንታዊ እንግሊዝኛ እያንዳንዱ ስም የተወሰነ ጾታ (ወንድ፣ ሴት ወይም ግዑዝ) ነበረው። ለምሳሌ sēo sunne /ሴዮ ሱነ/ (ፀሐይቱ) አንስታይ፣ se mōna /ሴ ሞና/ (ጨረቃው) ተባዕታይ፣ þæt wæter /ት ዋተር/ (ውኃው) ግዑዝ ነበር።

ጽሕፈት ለማስተካከል

ቋንቋው መጀመርያ ፉሶርክ በተባለው የሩን ፊደል ሲጻፍ ክርስትና ከተቀበለ በኋላ ግን በላቲን አልፋቤት ሊጻፍ ጀመረ። አንዳንድ ተጨማሪ ፈደላት እንዲህ ነበሩ:

  • ȝ - ይህ ፊደል (ከአይርላንድኛ ገብቶ) እንደ 'ይ' ወይም 'ግ' ወይም 'ኅ' ሊጠቀም ይችል ነበር።
  • ð - ይህ ፊደል ከላቲን d ተቀይሮ እንደ '' ወይም '' ሊጠቀም ይችል ነበር።
  • þ - ይህ ከቀድሞው ፉሶርክ ተገኝቶ ደግሞ እንደ '' ወይም '' ጠቀመ።
  • ƿ - 'W' የሚለው ፊደል ገና ስላልኖረ 'ው' ለመጻፍ በዚህ ፊደል (ከፉሶርክ ተገኝቶ) ነበር። በኋላ ዘመን ከp (ፕ) ጋር ስላለው ተመሳሳይነት ይህ ፊደል ጠፋ። ስለዚህ የዛሬ ሊቃውንት ጥንታዊ እንግሊዝኛ የሚጽፉት በዘመናዊው 'w' ነው።

ምሳሌ ለማስተካከል

የጌታ ጸሎት (አባታችን ሆይ) ለማስተካከል

Fæder ure þu þe eart on heofonum,
Si þin nama gehalgod.
To becume þin rice,
gewurþe ðin willa, on eorðan swa swa on heofonum.
urne gedæghwamlican hlaf syle us todæg,
and forgyf us ure gyltas, swa swa we forgyfað urum gyltendum.
and ne gelæd þu us on costnunge, ac alys us of yfele. soþlice.
ፋደር፡ ኡረ፡ ፡ ኤየርት፡ ኦን፡ ሄዮቮነም፣
ሲ፡ ን፡ ናማ፡ ይሃልጎድ።
ቶ፡ በኩመ፡ ን፡ ሪቸ፣
ይዉርን፡ ውላ, ኦን፡ ኤዮርን፡ ሷ፡ ሷ፡ ኦን፡ ሄዮቮነም።
ኡርነ፡ ይደይኋምሊቻን፡ ህላፍ፡ ሲውለ፡ ኡስ፡ ቶደይ፣
አንድ፡ ፎርዪውፍ፡ ኡስ፡ ኡረ፡ ዪውልታስ, ሷ፡ ሷ፡ ዌ፡ ፎርዪውቫ፡ ኡረም፡ ዪውልተንደም።
አንድ፡ ነ፡ ይለይድ፡ ፡ ኡስ፡ ኦን፡ ኮስትኑንገ, አክ፡ አሊውስ፡ ኡስ፡ ኦፍ፡ ኢውቨለ። ሶሊቸ።

ደግሞ ይዩ ለማስተካከል

የውጭ መያያዣዎች ለማስተካከል