አሉላ ዮሐንስ
አሉላ ዮሐንስ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ጊታር፣ ኪቦርድ፣ አርሞኒካ፣ ከበሮ (ድረም)ና ፒያኖን በደንብ የሚጫወት ሁለገብና ዘመናዊ አርቲስት ነው።[1]
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው አሉላ ዮሐንስ ዕድገቱ በአዳሪ ት/ቤት ውስጥ ነበር። በዚህ አዳሪ ት/ቤት ውስጥ እያለ የሙዚቃ ስሜት አድሮበት መጫወት ጀመረ።[1]
ከሙዚቃ መሳሪያዎች ጊታር በደንብ መጫወት የጀመረው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትንሽ እንደቆየ ነበር። በ፲፱፻፶ ዓ.ም. መጨረሻዎች ለትምህርት ወደ ጀርመን ሀገር ሄደ። ከዚያም ለሦስት ዓመት ተኩል የሕክምና ትምህርቱን ከተማረ በኋላ በማቋረጥ ወደ ኮንሰርቫቶሪ የሙዚቃ ት/ቤት ገባ። እዚህ የሙዚቃ ት/ቤት እያለም «Mr. President» /ሚስተር ፕሬዝዳንት/ የተባለውን የመጀመሪያውን ሸክላ አሳተመ።[1]
አሉላ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከሁለት አልበሞች በተጨማሪ አራት ሸክላዎች አሳትሟል። አሉላ በአሥራ አንድ ቋንቋዎች ይጫወታል። አማርኛ፣ ትግርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ስፓንኛ፣ ጣሊያንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ጀርመንኛና ዕብራይስጥኛ ወዘተ... አቀላጥፎ ይናገራል። ድሬዳዋ እያለ ስንታየሁ ይባል ነበር። «ስንታየሁ» የምትባለውም ሙዚቃ ከሕዝብ ጋር አስተዋወቀችው። አሉላ ከ፴ ዓመታት በላይ ረጅም የሙዚቃ ሕይወት ያለው አርቲስት ነው።[1]
ማጣቀሻ
ለማስተካከል- ^ ሀ ለ ሐ መ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 29". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.