ጃውሳ(cheaters, vagabonds, gangsters, vandalism, thief, Butchers, cannibalisms and Ambush  ማለት ያገኘውን የሚነጥቅ፣ ወንበዴ፣ዘራፊ፣ የሰው ነፍስ ነጣቂ፣ አውሬ ሰው በላ የሚል ትርጉም ይይዛል፡፡ ቃሉ ከአፋርና ከወሎ አከባቢ የተገኘ ሲሆን እጅግ በጣም አሰጠለ ጃውሳ ማለት ሽፍታ፣ ወንበዴ፣ ነጣቂ፣ ቀማኛ፣ በጎደጎደ ምድር በጨፈቀ ዱር እያደባ መንገድ ዐላፊውን እየደበደበ የሚቀማ ወንበዴ ማለት ነው .. ሌይሽመናይሲስ ወይም ሌይመኒዮሲስቁንጭር ማለት በሽታ የሚከሰተው በ ፕሮቶዞን  ፓራሳይት  ሌይሽመኒያ በሚባል ዝሪያ እና የሚዛመተውም በተወሰኑ የአሸዋ ዝንብ ዝሪያዎች ንክሻ ነው። [1] በሽታው በሶስት የተለያዩ መንገዶች ሊታይ ይችላል፦ ኩቴኒየስ፣ ሙኮኩቴኒየስ ወይም የውስጥ አካል ሌይሽመናይሲስ ሊሆን ይችላል። [1] ኩቴኒየስ የሚባለው በቆዳ ላይ ሽፍታዎችን/ቁስል በመፍጠር የታይ ሲሆን ሙኮኩቴኒየስ ከቆዳ ባሻገር አፍና አፍንጫንም ያቆስላል። የውስጥ አካል ኩቴኒየስ ደግሞ በቆዳ ላይ ሽፍታ ይጀምርና በመቀጠል ትኩሳት ያስከትላል፣ ቀይ የደም ሴል ቁጥርን ይቀንሳል፣ ጣፊያና ጉበተን ያሳብጣል። [1][2]

ሌይሽመናይሲስ
Classification and external resources

Cutaneous leishmaniasis in the hand of a Central American adult
ICD-10 B55
ICD-9 085
DiseasesDB 3266 29171
MedlinePlus 001386
eMedicine emerg/296
Patient UK ሌይሽመናይሲስ
MeSH D007896

በሽታው ሰዎችን የሚይዘው ከ20 ዓይነት በሚበልጡ የ ሌይሽመኒያ ዝሪያዎች አማካየነት ነው። [1] አጋላጭ ምክንያቶች፦ ድህነት፣ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ የደን መጨፍጨፍ አና የከተሞች መስፋፋት ናቸው። [1] ሦስቱንም የዚህ በሽታ ዓይነቶች ፓራሳይቱን አጉልቶ በሚያሳይ መሳሪያ/በማይክሮስኮፕ በማየት ማወቅ ይቻላል። [1] በተጨማሪም፤ ውስጣዊውን በሽታ በደም ናሙና ምርምራ ማወቅ ይቻላል። [2]

ሌይሽመኒያሲስን በተወሰነ ደረጃ ፀረ ተባይ ኬሚካልየተነከረ የአልጋ አጎበር አድርጎ በመተኛት መከላከል ይቻላል። [1] ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎች የአሸዋ ዝንቦችን ለመግደል የሚያስችል የኬሚካል ርጭት ማካሄድና በበሽታው የተያዙ ሰዎች በውቅቱ ህክምና እንዲያገኙ በማድረግ ስርጭቱን መግታት ነው። [1] የሚያስፈልገው የህክምና ዓይነት የሚወሰነው በሽታው ከምን እንደመጣ፣  በሌይሽመኒያዝሪያና በህመሙ ዓይነት ይወሳናል። [1] ለውስጣዊ በሽታ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት የመድኃኒት ዓይነቶች፦ ሊፖሶማል አምፎትሪሲን ቢ,[3] የ ፔንታቫሌንታንቲሞኒያልስ እና ፓሮሞምሲን ውህድ,[3] እና ሚልቴፎሲንናቸው። [4] ለኩቴኒየስ በሽታ ፓሮሞምሲን፣ ፍሉኮናዞል፣ ወይም ፔንታሚዲን ውጤታማ ሊሆን ይችላል። [5]

በአሁኑ ወቅት 12 ሚሊዮን የመሆኑ ሰዎች በ98 አገሮች [6] በበሽታው ተጠቅተው ይገኛሉ። [2] በየዓመቱ 2 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎእ አዲስ የሚያዙ ሲሆኑ [2] ከ20 እስከ 50 ሺ የሚሆኑት ደግሞ በየዓመቱ በዚህ ምክንያት ይሞታሉ። [1][7] ወደ 200 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በኢሲያ፣ አፍሪካ፣ ደቡብና መካከለኛ አሜሪካ፣ እንዲሁም ደቡብ አውሮፓ ለበሽታው ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ይኖራሉ። [2][8] የዓለም ጤና ድርጅት በሽታውን ለማከም በአንዳንድ መድኃኒቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ አድርጓል። [2] በሽታው በሌሎች በርካታ እንስሳት ላይ እንደ ውሾች እና አይጠ መጉጦችላይ ይከሰታል። [1]

ምንጮች ለማስተካከል

  1. ^ "Leishmaniasis Fact sheet N°375". World Health Organization (January 2014). በ17 February 2014 የተወሰደ.
  2. ^ Barrett, MP; Croft, SL  (2012). "Management of trypanosomiasis and leishmaniasis.". British medical bulletin 104: 175–96. doi:10.1093/bmb/lds031. PMID 23137768. 
  3. ^ Sundar, S; Chakravarty, J  (Jan 2013). "Leishmaniasis: an update of current pharmacotherapy.". Expert opinion on pharmacotherapy 14 (1): 53–63. doi:10.1517/14656566.2013.755515. PMID 23256501. 
  4. ^ Dorlo, TP; Balasegaram, M ; Beijnen, JH ; de Vries, PJ  (Nov 2012). "Miltefosine: a review of its pharmacology and therapeutic efficacy in the treatment of leishmaniasis.". The Journal of antimicrobial chemotherapy 67 (11): 2576–97. doi:10.1093/jac/dks275. PMID 22833634. 
  5. ^ Minodier, P; Parola, P  (May 2007). "Cutaneous leishmaniasistreatment.". Travel medicine and infectious disease 5 (3): 150–8. doi:10.1016/j.tmaid.2006.09.004. PMID 17448941. 
  6. ^ "Leishmaniasis Magnitude of the problem". World Health Organization. በ17 February 2014 የተወሰደ.
  7. ^ Lozano, R (Dec 15, 2012). "Global and regional mortality from 235 causes of death for 20 age groups in 1990 and 2010: a systematic analysis for the Global Burden of Disease Study 2010.". Lancet 380 (9859): 2095–128. doi:10.1016/S0140-6736(12)61728-0. PMID 23245604. 
  8. ^ Ejazi, SA; Ali, N  (Jan 2013). "Developments in diagnosis and treatment of visceral leishmaniasis during the last decade and future prospects.". Expert review of anti-infective therapy 11 (1): 79–98. doi:10.1586/eri.12.148. PMID 23428104.