ቴዲ አፍሮ

ኢትዮጵያውያን ዘፋኝ
(ከቴዎድሮስ ካሳሁን የተዛወረ)

ቴዲ አፍሮ (Teddy Afro) ዕውነተኛ ስሙ: ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ከዘመናችን ወጣት ኢትዮጵያውያን ዘፋኞችና አቀንቃኞች ሁሉ እጅግ ዝነኛ ነው። ቴዲ ለጃማይካዊው ሬጌ ኮከብ ቦብ ማርሊ የዘፈነለት የሬጌ ሙዚቃው በዓለም ዙሪያ እንዲታወቅ ያደረገው ሲሆን በተለይ ለኃይሌ ገብረ ሥላሴ ና ለሌላኛው የኦሊምፒክ ጀግና ቀነኒሳ በቀለኦሊምፒክስ ካሸነፉ በኋላ ያወጣቸው ወቅታዊ አልቡሞቹ ይበልጥ ታዋቂ አርገውታል። ቴዲ አፍሮን በጣም ታዋቂ ያደረግው 'ያስተሰርያል' የተባለው አልበሙ ሲሆን ስለ ፍቅር ፣ መቻቻል ፣ ህዝብ ስሜት እንዲሁም ስለመንግስታት እና ስለ ተቃዋሚዎች በፍቅር ለሃገር እድገት መስራት ዘፍኖአል። ዘፈኖቹ ብስል እና ጠንካራ ናቸው። ቴዎድሮስ ካሳሁን ከድምፃዊነትም በተረፈ የግጥምና ዜማም ደራሲ ሲሆን ከራሱ ስራዎች በተጨማሪ ለተለያዩ ድምፃዊያን የግጥም እና ዜማ ድረሰቶችን አበርክቷል። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሐምሌ 7 1968 በአዲስ አበባ ተወለደ። የትምህርት ደረጃ 12+ {{መለጠፊያ:Infobox musical artist|en}}

ቴዲ አፍሮ በሜልቦርንአውስትራሊያ (ጁን 2011 እ.ኤ.አ)

ቴዎድሮስ ካሳሁን ለምን "ቴዲ አፍሮ" ተባለ?

ለማስተካከል

ቴዲ አፍሮ የ፲፪ (12)ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ሰፊ ጊዜ ሥለነበረው ከመቸውም በተለየ ሁኔታ በዚያን ጊዜ ነበር በእግር በፈረስ ሥለ ሙዚቃ መጋለብ እና መሮጥ የጀመረው። ፲፱፻፺፩ (1991) አመተ ምህረት አካባቢ ከ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ ባለሙያዎች ላስታስ የተባለ የሙዚቃ ባንድ አቋቁመው ነበር:: በዚያን ጊዜ ቴዲ የራሱ የሆነ ባንድ እንዲኖረው ይፈልግ ሥለነበር ከሙያ ጉዋደኞቹ ጋር መመሆን በወቅቱ የነበሩትን ጥሩ ጥሩ የሙዚቃ መሳሪያዎች በመግዛት ላስታስ ከተባለው የሙዚቃ ባንድ ጋር አብሮ ለመሠራት ያላቸዉን ፍላጎት ለባንዱ አባላት ይገልፃሉ:: የባንዱ አባላትም በደስታ ይቀበሉዋቸዋል:: ብዙም ሳይቆዩ የባንዱ ስያሜ ከላስታስ ወደ አፍሮ ድምፅቀየሩት::

ባንዱንም በበላይነት በመቆጣጠር እና በመምራት ቴዲ ትልቅ ድርሻና ሃላፊነት ነበረው:: መሳሪያ ተጫዋቾቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁንሽዋንዳኝ ሃይሉ እና ግሩም መዝሙር የአፍሮ ሳውንድ ባለቤቶች ተብለው የሚጠቀሱ ሲሆን "ቴዲ ግን እንደ ባንዱ ባለቤት ብቻ ሣይሆን እንደ ቅርብ ጏደኛችን ነበር የምናየው" ይሉታል። እንግዲህ በዚሕ ጊዜ ነበር ቴዎድሮስ ካሣሁን የሚለው ስሙ በቴዲ አፍሮ ተተክቶ ዋነኛ መጠሪያ ስሙ ለመሆን የበቃው።

መኪና አደጋ

ለማስተካከል

በመኪና አደጋ ሰው ገድሎ በማምለጥ ወንጀል ተከሶ የነበረ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት 6 ዐመት አና 18000 ብር አንዲከፍል ከተወሰነበት በኋላ በእስር ቤት ውስጥ ለ 1 አመት ያህል ቆይቷል። ከዚያም በተለያዩ ምክንያቶች (ይቅርታን ይጨምራል) ከእስር እንዲፈታ ተወስኖለታል።

የፍርዱ ሁኔታ

ለማስተካከል

ፍርዱ ብዙውን ህዝብ አላሳመነም። ህዝቡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የቴዲን መፈታት አስመልክቶ ጩሀቱን አሰምቶአል። የፍርድ ሂደቱ ግልጽ አልነበረም ከ ወንጀል ክስነት ይልቅ የፖለቲካ ትርጉም የያዘ ነበር። እና ሌሎችም ተቃውሞዎች በተለያዩ ጊዜያት ከህዝቡ ተሰምተዋል። ሲገጭ አይቻለሁ ብሎ የመሰከረበት ይርዳው ጤናው ነው። እስከማለት ነበር የህዝቡ ተቃውሞ። waliya entertainment የተሰኘ youtube ቻናሌ ላይ ገብታችሁ ሙሉ መረጃውን ማግኘት ትችላላችሁ

ከእስር በኋላ

ለማስተካከል

ተዲ አፍሮ ከ እስር ከተፈታ በኋላ በተለያዩ ቦታዎች ትሪቶቹን አቅርቧል። በቀጣይም ሊያቀርባቸው ያሰባቸው ኮንሰርቶች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።


አለምአቀፍ ስኬት

ለማስተካከል

ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበሙ በ2009 ዓ.ም ለህዝብ በቀረበበት ወቅት በቢልቦርድ የአለም አቀፍ የሙዚቃ ሰንጠረዥ ላይ የአንደኛነት ደረጃን ተጎናፅፎ ነበር። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት [ባራክ ኦባማ] በየአመቱ ይፋ በሚያደርጉት የሙዚቃ ዝርዝር ውስጥም የቴዲ አፍሮ [አርማሽ ] የተሰኘውን ዜማ በ2021 እ.ኤአ ዝርዝር ውስጥ አካተው ነበር።