ውክፔዲያ:የማያደላ አስተያየት

የማያደላ አስተያየት (NPOV) ለማንም ቋንቋ ዊኪፔድያ ይፋዊና መሠረታዊ አቋም ነው። NPOV ከእንግሊዝኛው 'Neutral pont of view' ወይም ገለልተኛ አተያይ ማለት ነው።

የማያደላ አስተያየት ለመጣጥፍ እንዲኖር፥ ስለ ማንም አከራካሪ ጉዳይ ዋና ዋና አስተያየቶች ሁሉ ያለ አድልዎ መጻፍ አለባቸው። አንድ አስተያየት ቢኖር ከሌሎቹ አስተያየቶች በላይ ማስመስል አገባብ አይደለም። አስተያየቶቹ ሁሉ በሙሉና በገለልተኛ ቃላት ይገለጹ፣ እንጂ መጣጥፉ እራሱ ስለ አንድ ጉዳይ እንዳይከራክር ነው። ማን ምኑን እንዳመነ እና ለምን ለመግለጽ በፍጹም ጥሩ ዘዴ ነው። ለአንዱ ወገን ሀሣብ አድላዊ ክርክር መጻፍ ግን በመጣጥፍ ውስጥ አይፈቀድም። ከተጻፉት መረጃዎችና ትንትናዎች ሁሉ አንባብያን ምን ምን እንደሚያምኑ ለራሳቸው ይምረጡ እንደ ማለት ነው። ሆኖም በጥቂት ሰዎች ብቻ የተያዘ ሃሣብ በሰፊው እንደ ተያዘ ሃሣብ ክብደት አይሰጠም። በመጣጥፉም ውስጥ ለተገለጸው አስተያየት ሁሉ ዋቢ ምንጭ ባይገኝለት፣ ሌሎች አዛጋጆች ሲያውጡት ወይም ሲያስተካክሉት ተገቢ ነው።

ለአንድ መጣጥፍ የማያደላ አስተያየት መኖሩ አጠያያቂ ቢመስልዎ፥ ይህንን መለጠፊያ {{POV}} በገጹ ላይ መጻፍ ይችላሉ፦


ይህ መልጠፊያ ደግሞ መጣጥፉን ወደ መደብ:የማያደላ አስተያየት ጥያቄዎች ይጨምረዋል።

መጣጥፉ ለምን አጠያያቂ እንደ መሰለዎ በመጣጥፉ 'ውይይት ገጽ' ላይ መግለጫዎን ያቅርቡ። ከዚያ በኋላ በመወያየት በኩል የተሻለ ትክክለኛና የማያደላ አባባል ለመጣጥፉ በአዘጋጆቹ ስምምነት ወይም አስፈላጊ ከሆነ በዕርቅ ሊፈጠር ይቻላል።

ይህ መመሪያ የተወሰደው ከይፋዊ እንግሊዝኛው ትርጉም ነው።

ደግሞ ይዩ: ውክፔዲያ:Resolving disputes