ባሩክ ስፒኖዛ
ባሩክ ስፒኖዛ (ህዳር 24፣ 1632 – የካቲት 21፣ 1677) የደች ፈላስፋ ሲሆን አመጣጡም ከፖርቱጋል አይሁድ ቤተሰብ ነበር። ባሩክ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ታላላቅ የምክኑያዊነት ፈላስፋወች አንዱ እንደሆነ ስምምነት አለ። ሌሎች የዘመኑ ምክኑይዊነት አራማጆች ሌብኒዝ እና ደካርት ይጠቀሳሉ።
የህይወት ታሪክ
ለማስተካከልየስፒኖዛ አስተሳሰቦች በአይሁድ ህብረተሰብ ዘንደ የተጠላ ነበር። ስለሆነም በ1656 ከህብረተስቡ እንዲገለል ተደርጎ ነበር።
ቁልፍ ሐሳቦች
ለማስተካከልየስፒኖዛ ዋና ሃሳብ አምላክ እና ተፈጥሮ አንድ ናቸው የሚል ነበር። ተፈጥሮ ማለቱ እዚህ ላይ ማንኛው ህልው ነገር (ያለ ነገር) ይጠቀልላል። በጊዜው ይሰራበት የነበረውን የአዕምሮ እና አንጎል ክፍፍልን በመካድ ሁለቱም የአንድ አምላክ አዕላፍ ክፍላት አባል ናቸው አዋህዷል።
በተፈጥሮ ውስጥ ሰናይም ሆነ ዕኩይ የሆነ ነገር የለም ። ሰናይና እኩይ ትርጉም ያላቸው ለሰው ልጆች ብቻ ነው በማለት አስረድቷል። ለሰው ልጆች አንድ ኩነት (ክስተት) ሰናይ የሚሆነው ወደ ደስታ የሚመራው ሲሆን እና እኩይ የሚሆነው ደግሞ ለሃዘን ሲዳርገው ነው ብሎ አስረድቷል።
ስፒኖዛ ሁለት አይነት የሰው ልጅ አስተሳሰቦችንና ስሜቶችን ገልጿል፡
- አንደኛው ተነሳሽ ሲባል፣ አንድ ሰው ከራሱ አመንጭቶ የሚፈጽመውን ተግባር ይገልጻል። አንድን ሰው የራሱን ተግባር በበለጠ በተረዳ ቁጥር፣ የበለጠ ተነሳሽ ይሆናል። ተነሳሽ ስሜቶች ለደስታና አምላክን ለማወቅ እንዲሁም ነጻነትን ለመቀዳጀት ያበቃሉ።
- ሁለተኛው ፈዛዛ ሲባል፣ አንድ ሰው በሌሎች ሰወች ተፅዕኖ ስር ሲወድቅ ነው።
እንደ ስፒኖዛ አስተሳሰብ የሁሉ ሰው ግብ አምላክን በማወቅ መውደድ ነው (በሌላ አነጋገር፣ ተፈጥሮን በተቻለ መጠን ማውቅና መረዳት ነው)።