ቆፋሪዎቹ
ቆፋሪዎቹ (እንግሊዝኛ፦ Diggers /ዲገርዝ/) ከ1641 እስከ 1643 ዓ.ም. ድረስ በእንግሊዝ አገር የቆየ ኅብረተሠባዊ እንቅስቃሴ ነበረ። በ1641 በኦሊቨር ክሮምዌል ዘመን የመሠረተው ሳባኪው ጄራርድ ዊንስታንሊ ሲሆን ደንበኛ ስማቸው «ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» (/ትሩ ሌቨለርዝ/) ይባል ነበር። ሆኖም ከድርጊቶቻቸው የተነሣ «ቆፋሪዎቹ» ተብለው ይታወቁ ጀመር።
«ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» የሚለው ስያሜያቸው የመጣ ከሐዋርያት ሥራ 4፡32 ቃል[1] መሠረት የምጣኔ ሀብታቸው እኩልነት እምነት ስለ ነበራቸው። ቆፋሪዎቹ ርስትን በ«ማስተካከል» የቆየውን ኅብረተሠብ ለማሻሻል ሞከሩ። ዋና ሃሳባቸው በትንንሽ እርሻ ሰፈሮች ላይ በግብርና ሁላቸው እኩል ሆነው ለመኖር ነበር። በዚሁ ዘመን ከተነሡት ከእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ተቃራኒ እንቅስቃሴዎች አንዱ ናቸው።
1641 ዓ.ም. በእንግሊዝ አገር ኅብረተሠባዊ ሁከቶች የበዙበት አመት ነበር። የፓርላማ ወገን በጦር ሜዳ ላይ በሰፊው ድል አድርገው ቢሆንም የተሸነፈው ንጉሥ 1ኛ ቻርልስ ገና ስምምነት አልፈቀድም ነበር። በመጨረሻ ፓርላማና ሠራዊቱ እንደ አታላይ ይሙት በቃ ፈረዱበት።
የንጉሥ ጉባኤ በአዲስ መንግሥት ጉባኤ ወዲያው ተተካ። የፓርላማም ሥልጣን በጠብ ብዛት ስለ ተደከመ ይህ አዲስ ጉባኤ በሠራዊቱ ተገዛ። ብዙ ሰዎች በፖለቲካ ውስጥ ገብተው የአዲስ መንግሥት ለውጥ እንዴት እንደሚሻሻል ያላቸውን ልዩ ልዩ ሃሣቦቻቸውን እያቀረቡ ነበር። የቀደመውን ንጉሥ ልጅ 2ኛ ቻርልስ በዙፋን ላይ ማስቀመጥ የፈለጉ ወገን ሲኖር እንደ ክሮምዌል የነበሩት መሪዎች ደግሞ ባለ ሃብታሞች ብቻ የሚውከሉበት ፓርላማ ፈለጉ። በጆን ሊልቡርን መጻሕፍት ተጽእኖ የወጣ ተቃራኒ ወገን ደግሞ እያንዳንዱ አዋቂ ወንድ ባላቤት እንዲወከል እንጂ በሀብት መሠረት እንዳይሆን ጣሩ። እነኚህ «አስታካካዮቹ» (/ሌቨለርዝ/) ተባሉ። ከዚህ በላይ «አምስተኛው ንጉዛት ሰዎች» የሚባለው ወገን ሃይምኖታዊ መንግሥት (theocracy) ፈለጉ። ከነዚህ ወገኖች መካከል የዊንስታንሊ ቆፋሪዎች ሥርነቀል መፍትሔ አራመዱ።
ጄራርድ ዊንስታንሊና 14 ሌሎች እራሳቸውን ከአስተካካዮቹ ለመለየት ስማቸውን «ዕውነተኛ አስተካካዮቹ» ብለው አንድ ጽሑፍ አሳተሙ። ሃሳባቸውን ተግባራዊ አድርገው የጋራ መሬት ለማረስ ከጀመሩ በኋላ ሰዎች «ቆፋሪዎች» ይሉዋቸው ነበር። በቆፋሪዎቹ እምነት ተፈጥሮአዊ አኗርኗር አይነተኛ ነበረ። ዊንስታንሊ እንዳለው «ዕውነተኛ ነጻነት ሰው ምግቡንና ደህንነቱን ባገኘበት ይተኛል፣ ያውም በምድሪቱ ጥቅም ነው።»
በቆፋሪዎች አስተሳሰብ፣ ከኖርማኖች ወረራ (1058 ዓ.ም.) አስቀድሞ እንግሊዞች ቀና፣ ጻድቅ፣ እና በእኩልነት የኖረ ነገድ ሆነው ነበር። ኖርማኖች ከወረሩ በኋላ ግን መንግሥቱን በመያዛቸው መኳንንት ሆኑ፣ ኗሪ እንግሊዞች ግን ተራ ሕዝቦች ሆነው በኖርማኖች ሥር («የኖርማኖች ቀንበር») ተጨቆኑ። ዊንስታንሊ እንደ መሰለው የእንግሊዝ ንጉሥና የእንግሊዝ መንግሥት የኖርማኖች ተከታዮች ስለ ሆኑ መጣል ነበረባቸው።
ተግባር
ለማስተካከልቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታ፣ ወይብሪጅ፣ ሳሪ
ለማስተካከልበሚያዝያ 1641 ዓ.ም. ለመንግሥት ጉባኤ በቀረበው ደብዳቤ መሠረት፣ ብዙ ግለሠቦች በቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታ፣ ወይብሪጅ ላይ፣ በኮብሃም፣ ሳሪ ዙሪያ በጋራ መሬት ላይ አትክልትን ይተክሉ ጀመር፣ ይህም የምግብ ዋጋ ካለፈው ጊዜ ይልቅ ከሁሉ ከፍ ባለ ደረጃ ሲደርስ ነበር። የአቶ ሳንደርዝ ደብዳቤ እንዳወራው፣ «ሰው ሁሉ መጥቶ እንዲረዳቸው ሲለምኑ ምግብን፣ መጠትንና ልብስን በምላሽ እንዲያገኙ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።» አጥሮቹን ሁሉ በመፍረስ የዙሪያው ሕዝብ አንድ ላይ እንዲሠሩ ለማድረግ አሰቡ። በ10 ቀን ውስጥ ቁጥራቸው ብዙ ሺህ እንዲሆን አሳመኑ። «ዕቅድ በእጅ እንደ ያዙ የሚል ፍርሃት አለ።» በዚሁም ወር፣ ቆፋሪዎቹ «የእውነተኛ አስተካካዮቹ መርኅ ተራመደ» የሚባል ጽሑፍና አቤቱታ አሳተሙ።
በዙሪያው ባለርስቶች ጥያቄ፣ የአዲስ አራያ ሠራዊት አለቃ ሰር ቶማስ ፌይርፋክስ ከወታደሮች ጋር ደረሰና ዊንስታንሊንና ሌላ ቆፋሪ ዊልያም ኤቨራርድን በጥያቄ መረመራቸው። ኤቨራርድ ብርቱ ችግር እንደ ፈላ ስለ መሰለው ከእንቅስቃሰው ቶሎ ወጣ። ዳሩ ግን በፌይርፋክስ አስተያየት ቆፋሪዎች ጉዳት የሚያምጡ ስላልነበሩ፣ ባለርስቶቹ ጉዳዩን በችሎት እንዲቀጥሉት መከረ።
ዊንስታንሊ በሰፈሩ ላይ ቆየና ቆፋሪዎቹ ስላገኙት እንቅብቃቤ ለመጻፍ ቀጠለ። የርስቱ ጌታ ፍራንሲስ ድረይክ (ይህ የስመ ጥሩ ተጓዥ ፍራንሲስ ድረይክ አልነበረም) ሆን ብሎ በቅጥ ሊያሳድዳቸው ሞከረ። ወንበዶችን በቡድን አሰብስቦ ብዙ ጊዜ ከመደበደባቸው በላይ አንዴ የጋራ ቤታቸውንም አቃጠሉ። በችሎቱ ጉዳይ ቆፋሪዎች ለራሳቸው እንዳይመሰክሩ ተከለከለ። መረኑ የ«ዘላባጆቹ» (/ራንተርዝ/) ወገን አባላት ተብለው ተፈረደባቸው። (እንዲያውም ግን ዊንስታንሊ የዘላባጆች መሪ ላውረንስ ክላርክሶንን መረንንነትን ስለማስተማሩ ወቀሰው) በችሎቱ ጉዳይ ስለ ተሸነፉ፣ መሬቱን ለመልቀቅ እምቢ ካሉ ሠራዊት በእርግጥ ያስወጣቸው ነበር፤ ስለዚህ ለባለርስቶቹ ደስታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታን በነሐሴ 1641 ተዉ።
ሊተል ሂስ በኮብሃም፣ ሳሪ ዙሪያ
ለማስተካከልከቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሳደዱት ቆፋሪዎች መካከል አንዳንድ በትንሽ ርቀት ወደ ሊተል ሂስ ፈለሱ። 4.5 ሄክታር የመሬት ስፋት ልክ ታረሰ፤ ስድስት ቤቶች ታሠሩ፣ የበጋ ሰብል ተመረተ፣ አንዳንድ ጽሑፍ ታተመ። መጀመርያ በርኅራኄ ያያቸው የኮብሃም ርስቱ ጌታ ካህን ጆን ፕላት በኋላ ዋና ጠላታቸው ሆነ። በሥልጣኑ አማካይነት የዙሪያው ሕዝብ እንዳይረዳቸው አሰናከለ፤ እንዲሁም ቆፋሪዎቹም ሆነ ንብረታቸው በግፍ እንዲበደሉ አደረገ። በሚያዝያ 1642 ዓ.ም. ፕላትና ሌሎች ባለርስቶች ከርስታቸው በፍጹም አባረሯቸው።
ዌሊንግቦሮ፣ ኖርሳምቶንሺር
ለማስተካከልሌላ የቆፋሪዎች ሰፈር ደግሞ በዌሊንግቦሮ፣ ኖርሳምቶንሺር አካባቢ ቆመ። ይህ ማህበር በ1642 ዓ.ም. ያሳተመው አዋጅ እንዲህ ተባለ፦
- «እኛ የዌሊንግቦሮ መንደር በኖርሳምቶን ድኃ ኗሪዎች በይርሻንክ በተባለው በዌሊንግቦሮ ኗሪዎች ጋራ ወና ምድር ላይ ለመቆፈር፣ ለማዳበርና እህልን ለመዝራት ፈቅደን የጀመርንበት መሠረቶችና ምክንያቶች አዋጅ...»
ይህ ሠፈር የተጀመረው ከሳሪ ቆፋሪዎች ግንኙነት የተነሣ ይመስላል። በመጋቢት 1642 ከሳሪው ሰፈር የደረሱ 4 ተልእኮዎች በባኪንግሃምሸር ታሠሩ፤ የያዙትም ደብዳቤ በጄራርድ ዊንስታንሊና በሌሎች ቆፋሪዎች ተፈርሞ ሰዎች በየቦታው ለራሳቸው የቆፋሪ ሠፈር ለማቆምና የሳሪን ሰፈር በስንቅ ለመርዳት የሚል ልማኔ ነበር። «ፍጹም በየዕለቱ» የሚባለው ጋዜጣ እንደሚናግረው፣ እነኚህ ተልእኮዎች ከሳሪ ወደ ሚድልሴክስ፣ ህርትፎርድሺር፣ ቤድፎርድሸር፣ ባኪንግሃምሸር፣ ባርክሸር፣ ሃንቲንግደንሸር እና ኖርሳምቶንሸር አውራጃዎች ከተጓዙ በኋላ ታሠሩ።
በሚያዝያ 10 ቀን 1642 ዓ.ም. የመንግሥት ጉባኤ የኖርሳምቶንሸር ዳኛ አቶ ፔንትሎው በሚከተለው ችሎት «በአቅራቢያው ባሉት አስተካካዮች ላይ» ክስ እንዲያካሄድባቸው ታዘዘ። የአይቫ ቆፋሪዎች እንደ መዘገቡት፣ ከዌሊንግቦሮ ቆፋሪዎች 9 በወህኒ ታስረው ምንም ወንጀል በነርሱ ማረጋገጥ ባይቻልም ኖሮ ዳኛው ነጻ እንዳያስወጣቸው እምቢ ብለው ነበር።
አይቫ፣ ባኪንግሃምሸር
ለማስተካከልከሳሪና ከኖርሳምቶንሸር ሠፈሮች ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሌላ ቆፋሪዎች ሰፈር በአይቫ፣ ባኪንግሃምሸር ተገኘ። ይህም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ኮረብታ በ14 ኪ.ሜ ይርቃል። የአይቫ ቆፋሪዎች አዋጅ እንዳለው፣ ሌሎችም ሠፈሮች ደግሞ በባርኔት፣ ህርትፎርድሸር፣ በኤንፊልድ፣ ሚድልሴክስ፣ በዳንስተብል፣ ቤድፎርድሸር፣ በቦስዎርስ፣ ግሎስተርሸር እና እንዲሁም በኖቲንግሃምሸር ኖሩ። በተጨማሪ የሳሪ ሰፈር ከተሳደደ በኋላ፣ ቆፋሪዎቹ ልጆቻቸውን በአሳዳጊነት መተው እንደ ተገደዱ ይገልጻል።
የእንቅስቃሴው መጨረሻ
ለማስተካከልበመላ እንግሊዝ አገር የቆፋሪ ሰፈሮች በጠቅላላ ከጥቂት መቶ ሰዎች በላይ አልነበሯቸውም። በባለርስቶችና በመንግሥት ጉባኤ ማሳደድ ምክንያት እንቅስቃሴው በ1643 ዓ.ም. ጨረሰ።
ተጽእኖ
ለማስተካከልጽሑፎች
ለማስተካከል- Truth Lifting up its Head above Scandals («ዕውነት ከነውሩ በላይ ራሱን ሲያነሣ» - 1641 ዓ.ም.፤ ጄራርድ ዊንስታንሊ)
- The New Law Of Righteousness («የጽድቅ አዲስ ሕግ» - ጥር 1641፣ ጄራርድ ዊንስታንሊ)
- The True Levellers Standard A D V A N C E D: or, The State of Community opened, and Presented to the Sons of Men Archived ማርች 30, 2013 at the Wayback Machine («የዕውነተኛ አስተካካዮች መርኅ ተራመደ» - William Everard, John Palmer, John South, John Courton. William Taylor, Christopher Clifford, John Barker. Gerrard Winstanley, Richard Goodgroome, Thomas Starre, William Hoggrill, Robert Sawyer, Thomas Eder, Henry Bickerstaffe, John Taylor, &c. (April 20, 1649)
- A DECLARATION FROM THE Poor oppressed People OF ENGLAND, DIRECTED To all that call themselves, or are called Lords of Manors, through this NATION... («በእንግሊዝ አገር ከተጨቆኑት ድኆች ባለርስቶች ለተባሉት ሁሉ የደረሰው አዋጅ» - Gerrard Winstanley, John Coulton, John Palmer, Thomas Star ,Samuel Webb, John Hayman, Thomas Edcer, William Hogrill, Daniel Weeden, Richard Wheeler, Nathaniel Yates, William Clifford, John Harrison, Thomas Hayden, James Hall. James Manley, Thomas Barnard, John South, Robert Sayer, Christopher Clifford, John Beechee, William Coomes, Christopher Boncher, Richard Taylor, Urian Worthington, Nathaniel Holcombe, Giles Childe (senior), John Webb, Thomas Yarwel, William Bonnington. John Ash, Ralph Ayer, John Pra, John Wilkinson, Anthony Spire, Thomas East, Allen Brown, Edward Parret, Richard Gray, John Mordy, John Bachilor, William Childe, William Hatham, Edward Wicher, William Tench.(June 1, 1649).
- A LETTER TO The Lord Fairfax, AND His Councell of War, WITH Divers Questions to the Lawyers, and Ministers: Proving it an undeniable Equity, That the common People ought to dig, plow, plant and dwell upon the Commons, with-out hiring them, or paying Rent to any. On the behalf of those who have begun to dig upon George-Hill in Surrey. Gerrard Winstanly (June 9, 1649)
- A Declaration of The bloudie and unchristian acting of William Star and John Taylor of Walton (June 22, 1649), Gerrard Winstanley
- An Appeal To the House of Commons; desiring their answer: whether the common-people shall have the quiet enjoyment of the commons and waste land; ... (July 11, 1649), Gerrard Winstanley, John Barker, and Thomas Star
- A Watch-Word to the City of London, and the Armie (August 26, 1649), Gerrard Winstanley
- To His Excellency the Lord Fairfax and the Counsell of Warre the Brotherly Request of those that are called Diggers sheweth Archived ኤፕሪል 13, 2011 at the Wayback Machine (December 1649), John Heyman, An. Wrenn, Hen. Barton, Jon Coulton (in the behalf of others called the Diggers), Robert Cosler, John Plamer, Jacob Heard (in The Clarke Papers volume 2, [1894])
- To My Lord Generall and his Councell of Warr Archived ኤፕሪል 13, 2011 at the Wayback Machine (December 8, 1649), Gerrard Winstanley (in The Clarke Papers volume 2, [1894])
- The Diggers Song Archived ኤፕሪል 13, 2011 at the Wayback Machine (circa 1649,1650) (in the The Clarke Papers volume 2, [1894]), attributed to Gerrard Winstanley by the historian C. H. Firth, the editor of The Clarke Papers.
- The Declaration and Standard Of the Levellers of England, delivered in a speech to His Excellency the Lord Gen. Fairfax, on Friday last at White-Hall ..., William Everard
- Several Pieces gathered into one volume (1650, Preface dated December 20, 1649), A second edition of five of Gerrard Winstanley's works printed for Giles Calvert, the printer for nealy all the Diggers writings.[2]
- A New-yeers Gift FOR THE PARLIAMENT AND ARMIE: SHEWING, What the KINGLY Power is; And that the CAUSE of those They call DIGGERS (January 1, 1650), Gerrard Winstanley
- Englands Spirit Unfoulded or an incouragement to take the Engagement ... (Ca. February or March, 1650), Jerrard [sic] Winstanley.
- A Vindication of Those Whose Endeavors is Only to Make the Earth a Common Treasury, Called Diggers (March 4, 1650), Gerrard Winstanley
- Fire in the Bush (March 19, 1650), Gerrard Winstanley
- An appeale to all Englishmen, to judge between bondage and freedome, sent from those that began to digge upon George Hill in Surrey; but now are carrying on, that publick work upon the little heath in the parish of Cobham..., (March 26, 1650), Jerard [sic] Winstanley [and 24 others]
- A Letter taken at Wellingborough (March, 1650), probably written by Gerrard Winstanley.[3]
- An Humble Request, to the Ministers of both Universities, and to all Lawyers in every Inns-a-court (April 9, 1650), Gerrard Winstanley
- Letter to Lady Eleanor Davies (December 4, 1650), Gerrard Winstanley
- The Law Of Freedom in a Platform, or True Magistracy Restored (1652), Gerrard Winstanley
- ^ «ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።» --ግብረ ሐዋርያት 4፡32
- ^ Loewenstein, David (2001). Representing revolution in Milton and his contemporaries: religion, politics, and polemics in radical Puritanism (illustrated ed.). Cambridge University Press. p. 315. ISBN 0521770327.
- ^ Winstanley, Gerrard (2009). The complete works of Gerrard Winstanley. 2. Oxford University Press. p. 430. ISBN 0199576068.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |