ሄክታር
ሄክታር የአለም አቀፍ ክልል መለኪያ ሲሆን፣ ትርጉሙ በየጎኑ አንድ መቶ ሜትር ያለው ካሬ (አራት ማዕዘን ያለው) ክልል ስፋት ማለት ነው።
ቃሉ (በፈረንሳይኛ በኩል) የደረሰው ከግሪክኛ ἑκατόν /ሄካቶን/ «መቶ»፣ እና ሮማይስጥ area /አሬያ/ «ክልል» ነበር።
ሄክታር ስለዚህ አሥር ሺህ ካሬ ሜትር አለበት። ሄክታር በተለይ ለመሬት (ርስት ወይም እርሻ) ክልል ለመለካት ይጠቀማል።
-
1 ሄክታር = 10,000 ካሬ ሜትር
-
1 ሄክታር = የራግቢ ሜዳ የሚያህል ክልል፣ 100x100 m
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |