ስሪራቻ ከታይላንድ የመጣ፣ እንደ አዋዜ የመሰለ፣ የተቀመመ ወጥ አይነት ነው። የሚሠራው ከሚጥሚጣ፣ ሆምጣጤ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ስኳርና ጨው ሲሆን ለጤንነት መልካም ነው። ይኸው ጻዕም አሁን በተለይ በአሜሪካ አገር ዘመናዊነት አለው።
ስያሜው ከታይላንድ ከተማ ሲራቻ ሲሆን ይህም ከተማ ስም የደረሰው ከሳንስክሪት «ሽሪ ራጃ» («ቅዱስ ንጉሥ») ነው።